Dawit Tsige - Libe Sew текст песни
Исполнитель:
Dawit Tsige
альбом: Yene Zema
ልቤ ሰው ይወዳል
ልቤ ሰው ይወዳል ሰው
ልቤ ሰው ይወዳል ወዲያው ይላመዳል
የቀረበኝ ሁሉ ወዳጅ ይመስለዋል
ይላመዳል ሰው ያምናል ይወዳል
ይሄ ልቤ ሰው ያምናል ይወዳል
ይመስለዋል ወዳጅ ይመስለዋል
ይሄ ልቤ ሰው ያምናል ይወዳል
♪
አይቶ አለመራመድ እግሩን ቢያስነክሰው
በማጣት ቢያሳሹት እንዴት ይድናል ሰው
እሣት ከነደደ አመድ መቼ ይገዳል
ሰው ሁሉ እንደዚህ ነው አጥፊውን ይወዳል
ሰው ሁሉ እንደዚህ ነው አጥፊውን ይወዳል
♪
አንዳንዴ እንዲ ነው አንዳንዴ እንዲ ነው
ሰው ወዶ ሰው መጥላት ለካስ ፈተና ነው
ጥርስ አልሰንፍ አለ እንጂ ቀድሞ ለመሳቁ
እኔን ባይ አያጠፋም ተገፍተው ሲወድቁ
♪
ልቤ ሰው ይወዳል ወዲያው ይላመዳል
የቀረበኝ ሁሉ ወዳጅ ይመስለዋል
ይላመዳል ሰው ያምናል ይወዳል
ይሄ ልቤ ስው ያምናል ይወዳል
ይመስለዋል ወዳጅ ይመስለዋል
ይሄ ልቤ ሰው ያምናል ይወዳል
♪
ቀን ይዞ ቢጠልቅም ወዳጅ እንደ ጀምበር
ሰዉ ጨረቃ አያጣም ባመሸበት ሀገር
ልቤ አይጉደል እንጂ በሰዉ ያለ ተስፋን
በመጪው ይካሳል በሄደው የጠፋ
በመጪው ይካሳል በሄደው የጠፋ
♪
አንዳንዴ እንዲ ነው አንዳንዴ እንዲ ነው
ሰው ወዶ ሰው መጥላት ለካስ ፈተና ነው
አንዳንዴ እንዲ ነው እንዲ ነው አንዳንዴ
ሰው ወዶ መጥላቱን አይለምደውም ሆዴ
አዬዬዬዬዬዬ
ኧረ አይጣል ነዉ ኧረ አይጣል ነው
ኧረ አይጣል ነዉ ኧረ አይጣል ነው
ኧረ አይጣል ነዉ ኧረ አይጣል ነው
ኧረ አይጣል ነዉ ኧረ አይጣል ነው
አንዳንዴ እንዲ ነው አንዳንዴ እንዲ ነው
ሰው ወዶ ሰው መጥላት ለካስ ፈተና ነው
እይጠላውም አንዳንዴ እንዲ ነው
ለካስ ፈተና ነው እንዲ ነው አንዳንዴ
ሰው ወዶ መጠላቱን አይለምደውም ሆዴ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя