ስትተወኝ ተውኩ ራሴን
ጣልኩ እኔን ከፋው ውስጤን
ኀዘን በላኝ በቁሜ
ሳሳሁ ተለየኝ አቅሜ
ደስ ብሎኝ የምኖረው
የኔ ብትሆን ነው
ያንተን መርጠህ ሄደሀል
ምን ይመልስሀል
ስትተወኝ ተውኩ ራሴን
ጣልኩ እኔን ከፋው ውስጤን
ኀዘን በላኝ በቁሜ
ሳሳሁ ተለየኝ አቅሜ
ደስ ብሎኝ የምኖረው
የኔ ብትሆን ነው
ያንተን መርጠህ ሄደሀል
ምን ይመልስሀል
♪
አልታየኝም ነበር እንዲሁ እንደሚቀር
ስንቱን የሆንኩለት ያ ፍቅር
ያጎበዝኩት ልብህ ሳታምን ስትፈራ
በቃ ለ'ኔም ከ'ንግዲህ አይራራ
(ይሁን ይሁን)
አስበልጠህ ፍቅርን ከ'ኔ መልካምነት
(ይሁን ይሁን)
ስትተወኝ ብጎዳም አልለውም ክህደት
(ይሁን ይሁን)
መውደዴ ይኖራል ስትቀር አይቀርም
(ይሁን ይሁን)
ወደሀት ነውና እኔ አልቀየምህም
አልታየኝም ነበር እንዲሁ እንደሚቀር
ስንቱን የሆንኩለት ያ ፍቅር
ያጎበዝኩት ልብህ ሳታምን ስትፈራ
በቃ ለ'ኔም ከ'ንግዲህ አይራራ
(ይሁን ይሁን)
አስበልጠህ ፍቅርን ከ'ኔ መልካምነት
(ይሁን ይሁን)
ስትተወኝ ብጎዳም አልለውም ክህደት
(ይሁን ይሁን)
መውደዴ ይኖራል ስትቀር አይቀርም
(ይሁን ይሁን)
ወደሀት ነውና እኔ አልቀየምህም
♪
ስትተወኝ ተውኩ ራሴን
ጣልኩ እኔን ከፋው ውስጤን
ኀዘን በላኝ በቁሜ
ሳሳሁ ተለየኝ አቅሜ
ደስ ብሎኝ የምኖረው
የኔ ብትሆን ነው
ያንተን መርጠህ ሄደሀል
ምን ይመልስሀል
♪
ሰው በሚያሻህ ጊዜ ስለኖርኩ ከጎንህ
አልልም መዋሌ ይክበድህ
የልብህን ሰምተህ ከ'ኔ እሷን መምረጥህ
አያስወቅስህም ልክ ነህ
(ይሁን ይሁን)
አስበልጠህ ፍቅርን ከ'ኔ መልካምነት
(ይሁን ይሁን)
ስትተወኝ ብጎዳም አልለውም ክህደት
(ይሁን ይሁን)
መውደዴ ይኖራል ስትቀር አይቀርም
(ይሁን ይሁን)
ወደሀት ነውና እኔ አልቀየምህም
የፍቅሬን ውለታ ካንተ ባላገኝም
ያደረግኩልህ አይቆጨኝም
የመልካምነቴን እሸለመዋለሁ
ፍቅር ይደርሰኛል አውቃለሁ
(ይሁን ይሁን)
አስበልጠህ ፍቅርን ከ'ኔ መልካምነት
(ይሁን ይሁን)
ስትተወኝ ብጎዳም አልለውም ክህደት
(ይሁን ይሁን)
መውደዴ ይኖራል ስትቀር አይቀርም
(ይሁን ይሁን)
ወደሀት ነውና እኔ አልቀየምህም
ደስ ብሎኝ የምኖረው
የኔ ብትሆን ነው
ያንተን መርጠህ ሄደሀል
ምን ይመልስሀል
ደስ ብሎኝ የምኖረው
የኔ ብትሆን ነው
ያንተን መርጠህ ሄደሀል
ምን ይመልስሀል
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя