ቀን ቀን ስራ አይጠፋም
አስሮ የሚያውለኝ
የማያስተክዘኝ የማያሳስበኝ
ሲመሽ ግን አልችልም ሰማዩ ሲጠቁር
ድቅን ይልብኛል ያሳለፍነው ፍቅር
ሲመሽ እደክማለው ይመጣል ትዝታህ
የማይደበዝዘው የማያልቅ ናፍቆትህ
♪
የኑሮ ዱብ ዱብ ቀን ቀን ይይዘኛል
ግን መምሸቱ አይቀርም ማን አለሁ ይለኛል
ሲመሽ ይታመማል መላው ሰውነቴ
የምወደውን ሰው አንተን በማጣቴ
ቀን ቀን ሰው አላጣም የሚያስተዛዝነኝ
የሚሆን ከጎኔ የሚያጨዋውተኝ
ሲመሽ ግን ችግር ነው ስሆን ለብቻዬ
ትዝ ትለኛለህ ማልቀስ ነው ስራዬ
ሲመሽ እደክማለው ይመጣል ትዝታህ
የማይደበዝዘው የማያልቅ ናፍቆትህ
♪
የኑሮ ዱብ ዱብ ቀን ቀን ይይዘኛል
ግን መምሸቱ አይቀርም ማን አለው ይለኛል
ሲመሽ ይታመማል መላው ሰውነቴ
የምወደውን ሰው አንተን በማጣቴ
ቀን ቀን እስቃለው ያለህ ይመስለኛል
ሲመሽ ግን እውነቱ ይገለጥልኛል
ሲመሽ አይ ስቃዬ ሆዴ ይረበሻል
ሀሳቤ እኔን ትቶ ወዳ'ንተ ይነጉዳል
ምንአይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መዋደድ
በጊዜ መራዘም በርቀት የማይበርድ
ምንአይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መዋደድ
በጊዜ መራዘም በርቀት የማይበርድ
ምንአይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መዋደድ
በጊዜ መራዘም በርቀት የማይበርድ
ምንአይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መዋደድ
በጊዜ መራዘም በርቀት የማይበርድ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя