Kishore Kumar Hits

Genene Haile - Semayawi текст песни

Исполнитель: Genene Haile

альбом: Negem Lela Qen New


በእውነት በቃ አንቺው ነሽ ልቤ አጊኝቶሻል
የውበት ሠገነት ሆነሽ ልቤን ማርከሻል
ስላንቺ አረ ስንቱን ስንቱን እላለሁ
የፍቅር መገለጫ ነሽ አደንቅሻለሁ
ካንቺ በቀር አያሻማኝ ለአይኔ ሞልቶ ሌላ
የኔ ገላ ሆነሽ የልቤ አጥር ከለላ
ማን ይታየኛ ታዲያ ሌላ
ሙዚቃዊ የቃል ለዛዎችሽ ትርጉማቸው
ፍቅር ናቸው
ላየ ላዩን ሳይሆን የውስጥሽን የገለፁልኝ ውበትሽን
ሌላ ወዶ አይላላም ልቤ
ሌላ ምን አይቶ ሌላ
ሌላ ደስታ ጭራሽ አይፈልግ
ለምዶ ያላንቺስ ገላ
በእውነት በቃ አንቺው ነሽ ልቤ አጊኝቶሻል
የውበት ሠገነት ሆነሽ ልቤን ማርከሻል
ስላንቺ አረ ስንቱን ስንቱን እላለሁ
የፍቅር መገለጫ ነሽ አደንቅሻለሁ
እልሻለሁ ካንቺ ጋራ ሆኜ ማሳለፌ
የቅሌት ህልሜ ባንቺ ሲፈታ ያየሁት ጎኔ
የልቤን ንግስት ለኔው ሾሜ
ቤተልሄም የገነት አምሳያ ሰላማዊ
ነው ተፈጥሮሽ ህብረቀለማቱን ያደለሽ
ልክ እንደ ፀጋ ሠማያዊ
ሌላ ወዶ አይላላም ልቤ
ሌላ ምን አይቶ ሌላ
ሌላ ደስታ ጭራሽ አይፈልግ
ለምዶስ ያላንቺስ ገላ
ሌላ ወዶ አይላላም ልቤ
ሌላ ምን አይቶ ሌላ
ሌላ ደስታ ጭራሽ አይፈልግ
ለምዶስ ያላንቺስ ገላ
ሌላ ወዶ አይላላም ልቤ
ሌላ ምን አይቶ ሌላ
ሌላ ደስታ ጭራሽ አይፈልግ
ለምዶስ ያላንቺ ገላ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители