መችም ካልታደልኩኝ ቀርቤ ላዋይሽ
ከጀርባሽ ያዉለኝ በቃ እንደ እንስራሽ
ዘወትር በእንስራሽ እንደምትጨልፊዉ
ልቤንም በፍቅርሽ ምን አለ ብትቀዝፊዉ
መችም ካልታደልኩኝ ቀርቤ ላዋይሽ
ከጀርባሽ ያዉለኝ በቃ እንደ እንስራሽ
ዘወትር በእንስራሽ እንደምትጨልፊዉ
ልቤንም በፍቅርሽ ምን አለ ብትቀዝፊዉ
ብልሁ አሳ አጥማጅ አስቦ የችለቱን
ነበረ ከኩሬዉ ከንዙ አፋፋፍ ላይ የቀለሰዉ ቤቱን
እኔም አጠምዳለዉ መረቤም አይኔ ነዉ
ባላጠምድሽ እንኳን ጐጆዬን ቀልሼ ሳይሽ እኖራለዉ
እንስራሽን አድርጎ ቢፈጥረኝ
ምን ነበር ከጀርባሽ ቢያዉለኝ
ሰማይ ጠርቶ ወፎች እስኪንጫጩ
አቤት ጭንቄ እስክሄድ ወደ ምንጩ
እንስራሽን አድርጎ ቢፈጥረኝ
ምን ነበር ከጀርባሽ ቢያዉለኝ
ሰማይ ጠርቶ ወፎች እስኪንጫጩ
አቤት ጭንቄ እስክሄድ ወደ ምንጩ
መችም ካልታደልኩኝ ቀርቤ ላዋይሽ
ከጀርባሽ ያዉለኝ በቃ እንደ እንስራሽ
ዘወትር በእንስራሽ እንደምትጨልፊዉ
ልቤንም በፍቅርሽ ምን አለ ብትቀዝፊዉ
መችም ካልታደልኩኝ ቀርቤ ላዋይሽ
ከጀርባሽ ያዉለኝ በቃ እንደ እንስራሽ
ዘወትር በእንስራሽ እንደምትጨልፊዉ
ልቤንም በፍቅርሽ ምን አለ ብትቀዝፊዉ
ዛሬስ በድኔ ነዉ ከአልጋዉ ላይ የዋለዉ
እሷን እያሰበ ጭንቀት እጠገባዉ ልቤ ወንዙ ዛር ነዉ
እንደ ጥሩ አሳ አጥማጅ ከወንዙ ዳርቻ
አይን አይኗን እያየዉ ቤቴን ልቀልሰዉ ልስራ መሰንበቻ
እንስራሽን አድርጎ ቢፈጥረኝ
ምን አለ ከጀርባሽ ቢያዉለኝ
ሰማይ ጠርቶ ወፎች እስኪንጫጩ
አቤት ጭንቄ እስክሄድ ወደ ምንጩ
እንስራሽን አድርጎ ቢፈጥረኝ
ምን ነበር ከጀርባሽ ቢያዉለኝ
ሰማይ ጠርቶ ወፎች እስኪንጫጩ
አቤት ጭንቄ እስክሄድ ወደ ምንጩ
ብልሁ አሳ አጥማጅ አስቦ የችለቱን
ነበረ ከኩሬዉ ከንዙ አፋፋፍ ላይ የቀለሰዉ ቤቱን
እኔም አጠምዳለዉ መረቤም አይኔ ነዉ
ባላጠምድሽ እንኳን ጐጆዬን ቀልሼ ሳይሽ እኖራለዉ
እንስራሽን አድርጎ ቢፈጥረኝ
ምን ነበር ከጀርባሽ ቢያዉለኝ
ሰማይ ጠርቶ ወፎች እስኪንጫጩ
አቤት ጭንቄ እስክሄድ ወደ ምንጩ
እንስራሽን አድርጎ ቢፈጥረኝ
ምን ነበር ከጀርባሽ ቢያዉለኝ
ሰማይ ጠርቶ ወፎች እስኪንጫጩ
አቤት ጭንቄ እስክሄድ ወደ ምንጩ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя