Kishore Kumar Hits

Nhatty Man - Anchin Say текст песни

Исполнитель: Nhatty Man

альбом: Vol. ፪


አንቺን ያየ
ባንቺ አይን
እያደር ዘመን በህይወቴ የልቤን ጥያቄ
ባንቺ መልስ አግኝቷል በዝቷል መደነቄ
በምክንያት መሀል ያጠፋኝ ምክንያት
ሲያወጣኝ አየሁ ከደበቀኝ ምራት
ሀገርሽ ሀገሬ ባይሆን ያደግኩበት
ሲቀረኝ ተሰማኝ ፍቅር ባለው ምህረት
እልፍ ከሆነ ነገር በእድሜዬ ካየሁት
ያንቺ በዝቶልኛል የለኝም ያጣሁት
አንቺን ሳይ ... አየሁሽ ባንቺ ላይ _
ሀገር ይታየኛል ... ብዙ እኔን የሆነ
ፍቅር ይታየኛል ... ሰላም ያሰፈነ
እውነት ይታየኛል ... ቅንነት ያዘለ
ቋንቋ ይሰማኛል... አንደበት ያየለ _
የልቤ ምቱ ዜማው ሲገጥም
ታየኝ ዘመኔ ባንቺ መኖር ሲጥም
በፍቅር አድሰሽ ደስታን ሞላሽው
ዳግም በረታ አነሳሽው
ባንቺ አይን ተስፋን እያየው
ልቤ ጨከነ ... አው
ትርጉም አልባው ነገር ማሰብ የተሳነኝ
ያበረታኝ ጀመር ባንቺ እየታየኝ
ልቤ ተማመነ ሀሳቡን ጣለብሽ
ተለየሽ ከሌላው ወዶ አነገሰሽ
አንቺን ሳይ ... አየሁሽ ባንቺ ላይ _
ሀገር ይታየኛል ... ብዙ እኔን የሆነ
ፍቅር ይታየኛል ... ሰላም ያሰፈነ
እውነት ይታየኛል ... ቅንነት ያዘለ
ቋንቋ ይሰማኛል ... አንደበት ያየለ _
የልቤ ምቱ ዜማው ሲገጥም
ታየኝ ዘመኔ ባንቺ መኖር ሲጥም
በፍቅር አድሰሽ ደስታን ሞላሽው
ዳግም በረታ አነሳሽው _
አየሁሽ ባንቺ ላይ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Man

2013 · альбом

Похожие исполнители