ገዳይ ገዳይ ገዳዬ በፍቅር በፍቅር ገዳይ
ገዳይ ገዳይ ገዳዬ በመውደድ በመውደድ ገዳይ
ከተሰናዳልህ ልቤም እንደ ቤቴ
አደራ ና ስልህ ጎራ በል በሞቴ
ከተሰናዳልህ ልቤም እንደ ቤቴ
አደራ ና ስልህ ጎራ በል በሞቴ
♪
እንኳን እኔን እና መውደድህ ልቤን ያሸፈተው
ዓይንህን በስስት ሁልጊዜ የምመለከተው
ሰው ቢሆን ጨረቃ ኮኮቡ ዝናህን ሲሰማ
ላንተ ረግፎ ነበር ሰማዩ ትቶ ለጨለማ
ዝና ዓለሜ አቤት የሱ ስራ
አያልቅበት መቼም አያባራ
ሽሙንሙኔ እንደምን አበጀህ
አንተን ከእኔ ያወዳጀህ
ዝና ዓለሜ አቤት የሱ ስራ
አያልቅበት መቼም አያባራ
ሽሙንሙኔ እንደምን አበጀህ
አንተን ከእኔ ያወዳጀህ
ዝናዓለም ዝናዬ ልበልህ ዝናር
ጣፈጠኝ ዋ ስምህ ልክ እንደ ማር
አንተ ልጅ ዝናዬ ልበልህ ዝናር
ጣፈጠኝ ዋ ስምህ ልክ እንደ ማር
♪
ገዳይ ገዳይ ገዳዬ በፍቅር በፍቅር ገዳይ
ገዳይ ገዳይ ገዳዬ በመውደድ በመውደድ ገዳይ
ከተሰናዳልህ ልቤም እንደ ቤቴ
አደራ ና ስልህ ጎራ በል በሞቴ
ከተሰናዳልህ ልቤም እንደ ቤቴ
አደራ ና ስልህ ጎራ በል በሞቴ
♪
በቀስተደመና ውብ ቀለም በተኳለው ሰማይ
የዘገየ እንግዳ ተብላ ብቅ እንዳለች ፀሀይ
አየህ ወይ ተፈጥሮ ውበቷን ከዓይንህ ላይ ስትስል
አለ ወይ በምድር ሰው ለእኔ የአንተን ሩብ ያህል
ዝና ዓለሜ አቤት የሱ ስራ
አያልቅበት መቼም አያባራ
ሽሙንሙኔ እንደምን አበጀህ
አንተን ከእኔ ያወዳጀህ
ዝና ዓለሜ አቤት የሱ ስራ
አያልቅበት መቼም አያባራ
ሽሙንሙኔ እንደምን አበጀህ
አንተን ከእኔ ያወዳጀህ
ዝናዓለም ዝናዬ ልበልህ ዝናር
ጣፈጠኝ ዋ ስምህ ልክ እንደ ማር
አንተ ልጅ ዝናዬ ልበልህ ዝናር
ጣፈጠኝ ዋ ስምህ ልክ እንደ ማር
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя