ምሣሌ አምሳል ምን አል ላ'ንቺማ
ላረግሽው ምግባር ከቶ ሚስማማ
ቢመነዘርም ባለም ካለው
አንቺነትሽን ለኔ አይገልፀውም
አይገልፀውም አይገልፀውም
አይገልፀውም አይገልፀውም
ያንስብኛል ይሳሳል ለኔ
ሆሄ ፊደላት ሰዋሰው ቅኔ
ውበት ቁንጅናሽ በምን ይለካ
በማን ጠርቼሽ ምን ብዬ ልርካ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገር ለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
ቀንቶኝ እድሌ ደርሶኝ በተራ
በፍቅርሽ ብርሀን ቀኔ ሲበራ
ማሞገሻ ቃል ላገኝ ብለፋ
ፈልጌ አጣሁኝ ስያሜሽ ጠፋ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገር ለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገር ለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
እፍኝ ማይሞላ እድሜዬ በዝቶ
ዜማው አምሮልኝ ባንቺው ተቃኝቶ
መንገዴ ቀና ሂወቴ ሙሉ
አንቺ ካለሽኝ ተድላ ነው ሁሉ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገርለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
ባንቺ ሁሉ አለኝ ደስ ደስ
እንግዳ ሆንኩኝ ለዓለም እንዳዲስ
ብቸኝነቴን ባንቺ ኮንኜ
በፍቅርሽ ድኬ ቆምኩኝ ሰው ሆኜ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገር ለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገር ለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
እንደው ነፍስ ነገር ለኔ
ውቤ ውቤ ውቤ ውቤ
እንደው ነፍስ ነገር ላይኔ
ማሬ ማሬ ማሬ ማሬ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя