Kishore Kumar Hits

Esubalew Yetayew - Photo Yinageral текст песни

Исполнитель: Esubalew Yetayew

альбом: Tertaye


#ፎቶ_ይናገራል
ከፎቶሽ ላይ ባየው መልክሽ ውበት ቁንጅናሽን
ሳትነግሪኝ ነገረኝ ምስልሽ ለኔ መኖርሺ
ወዝሽን ጨልፈሽ ለኔ መስጠትሺ
ቁንጅናሽን ኣጥተሽ ቆንጆ ማረግሺ
የፊትሽ ቁንጅና ገረመኝ የጥርስሽ ንፃቱ
ዛሬ ካንቺ ባጣው የኔ አለም አመመኝ በብርቱ
ነብስ ሳውቅ ሆነና ነገሩን ሳጤነው ቆይቼ
ከኔ ፊት አየሁት መልክሽን ካንቺ ላይ አጥቼ
ውበትሺን ያጣሺው እማ ስትወልጂኝ ነው
ላረግሺልኝ ነገር የኔ አቅም አንድ ነው
እወድሻለሁ (×8)
ከፎቶ ላይ ባየው መልክህ ግርማ ሞገስህን
ሳትነግረኝ ነገረኝ ምስልህ ለኔ መኖርህን
ጎንብሰህ ወገብክን እኔን ማቅናትህን
ቤት ቤትህን ስትል ውጪውን መጥላትህ
ያፍሮ ፀጉርህ ጥቁረት ይገርማል የገፅህ ማማር
ወንዳወንድነትህ ጌትዬ የጥርስህ ድርድር
አንተ ባታወራው ባይቀናህ ምስልህም ያወራል
ለልጆችህ ስትል መኖርክን ፎቶህ ይናገራል
ሞገስክን ያጣኸው አባ ስትወልደኝ ነው
ላረክልኝ ነገር የኔ አቅም አንድ ነው
እወድሃለሁ! (×6)
እወድሻለሁ!
እወድሻለሁ!
እወድሃለሁ!
እወድሃለሁ!
እወድሻለሁ!
እወድሻለሁ!
እወድሃለሁ!
እወድሃለሁ!
I cannot tell you how much I love you, dad.
You have sacrificed so much for us and I can never be able
To match up to that ever in my life. I love you so much, papa.
HAPPY FATHERS DAY!
እወድሻለሁ!
እወድሻለሁ!

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители