ተኩስ ወዳጄ ተኩስ ተኩስ
በተስፋ ጥይት ተኩሰህ ጀግን
ሽንፈትህን ድል ንሳው
እጅ እንዳትሰጥ አደራ
አደራ
ተኩሰህ በለው
ተኩስ ወዳጄ ተኩስ
ግድ የለም ተኩስ ተኩስ
እስኪያልቅ ጥይትህ
እስከ ጫፍ ጥፍ ጣፊ
ጠብታ ተስፋ
መውደቅ መነሳት ነው እስካሉ በአለም
በቃ ብሎ ነገር በምድር ላይ የለም
ግድ የለም ተኩስ ተኩስ
እስኪያልቅ ጥይትህ
እስከ ጫፍ ጥፍ ጣፊ
ጠብታ ተስፋ
አንዱ ጫፍ ሌላን ሲጀምር
ምሽት በንጋት ሲበሰር
መስከረም አሀዱ የሚባለው
ጳግሜ ጎዶሎ ታልፎ ነው
አንዱ ጫፍ ሌላን ሲጀምር
ምሽት በንጋት ሲበሰር
መስከረም አሀዱ የሚባለው
ጳግሜ ጎዶሎ ታልፎ ነው
አበቃ በቃ በቃ
የለም አበቃ
አበቃ በቃ በቃ
የለም አበቃ
ቀን ቢከፋ ሊሻር ቀን ቆጥሮ
ለሁሉ ጊዜ አለው ቀጠሮ
ተስፋህ ነው የነገ አለም
ተፈጸመ አበቃ የለም
ቀን ቢከፋ ሊሻር ቀን ቆጥሮ
ለሁሉ ጊዜ አለው ቀጠሮ
ተስፋህ ነው የነገ አለም
ተፈጸመ አበቃ የለም
አበቃ በቃ በቃ
የለም አበቃ
አበቃ በቃ በቃ
የለም አበቃ
ግድ የለም ተኩስ ተኩስ
እስኪያልቅ ጥይትህ
እስከ ጫፍ ጥፍ ጣፊ
ጠብታ ተስፋ
ግድ የለም ተኩስ ተኩስ
እስኪያልቅ ጥይትህ
እስከ ጫፍ ጥፍ ጣፊ
ጠብታ ተስፋ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя