Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal текст песни
Исполнитель:
Gossaye Tesfaye
альбом: Siyamish Yamegnal
አንቺ ሲያምሽ ውሎ ካደረ
የኔስ ልብ ረግቶ ምኑን ኖረ
ያንቺ ጤና ሲጎል የኔም ይጎላል
የነገው ሰላሜም ይታጎላል
አንቺ ሲያምሽ ውሎ ካደረ
የኔስ ልብ ረግቶ ምኑን ኖረ
ያንቺ ጤና ሲጎል የኔም ይጎላል
የነገው ሰላሜም ይበተናል
♪
በይ ኑሪልኝ ለኔ ከጭንቀት ከስቃይ
እፎይ ብለሽ ከጎኔ
ግድ ይለኛል መውደዴ አንጀቴ ሆዴ
ደርሶ አይንካሽ ክፋ
ፀጋ በረከቱ ያዝንብልሽ በጤና
ከዚ በላይ የምለው ምንስ አለ
ጎኔን አመመኝ ስትይ እኔንም ይሰማኛል
ልቤን ተሰማኝ ስትይ የኔም ልብ ይሸበራል
ያንቺን ስቃይ የኔ ያርገው
ከማለት ሌላ ቃል የለኝም በእውነት
አይንካሽ ክፋ አትታመሚ
በይ ተነሺልኝ በይ ቀና ቀና
ባንቺው የያዝኩት የህይወት ጉዞ
ተጀመረ እንጂ መች አለቀና
አይንካሽ ክፋ አትታመሚ
በይ ተነሺልኝ በይ ቀና ቀና
ገና ያልኖርነው ብዙ ይታየኛል
ደና ነኝ በይኝ ሲያምሽ ያመኛል
♪
አንቺ ሲያምሽ ውሎ ካደረ
የኔስ ልብ ረግቶ ምኑን ኖረ
ያንቺ ጤና ሲጎል የኔም ይጎላል
የነገው ሰላሜም ይበተናል
♪
ማልዶ ሌት ሳይነጋ ፈጣሪን
በፀሎት የሚማፀነው አንደበትሽ
ይተርፍየልዎይ ካንቺ አልፎ ለኔ አፍቃሪሽ
ደርሶ አይንካሽ ክፋ
ፀጋ በረከቱ ያዝንብልሽ በጤና
ከዚ በላይ የምለው ምንስ አለና
ጎኔን አመመኝ ስትይ እኔንም ይሰማኛል
ልቤን ተሰማኝ ስትይ የኔም ልብ ይሸበራል
ያንቺን ስቃይ የኔ ያርገው
ከማለት ሌላ ቃል የለኝም በእውነት
አይንካሽ ክፋ አትታመሚ
በይ ተነሺልኝ በይ ቀና ቀና
ባንቺው የያዝኩት የህይወት ጉዞ
ተጀመረ እንጂ መች አለቀና
አይንካሽ ክፋ አትታመሚ
በይ ተነሺልኝ በይ ቀና ቀና
ገና ያልኖርነው ብዙ ይታየኛል
ደና ነኝ በይኝ ሲያምሽ ያመኛል
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя