እንዴት እሆን ነበር
ከስደት ጋር ሆደ ባሻው እኔ
ምን ይውጠኝ ነበረ
በሰው ሀገር ባትኖሪ ከጎኔ
አልችለም ነበረ ብቻዬን ላድር
ጠቅልዬ ልኖር
ፍቅርሽ ባይሆነኝ አጋር
እንዴት እሆን ነበር
ከስደት ጋር ሆደ ባሻው እኔ
ምን ይውጠኝ ነበረ
በሰው ሀገር ባትኖሪ ከጎኔ
አልችለም ነበረ ብቻዬን ላድር
ጠቅልዬ ልኖር
ፍቅርሽ ባይሆነኝ አጋር
ከኑሮ ሸክም ጋር ሲጫን ብቸኝነት
ሲነሳ ጤንነት
አይጣል የሰው ሀገር ወፈፍ የሚያደርገው
ጭምት የሚያብድበት
የሰው ፊት ወላፈን ሲፈጅ ግርፋቱ
ባይተዋርነቱ
ብለሽ ካንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ
ባንቺው ቆሟል ቤቱ
እያፅናናሽ እያረጋጋሽኝ የምታረሳሺኝ
የትም የትም አንድ ነሽ ያለሺኝ
እያፅናናሽ እያረጋጋሽኝ የምታረሳሺኝ
የትም የትም አንድ ነሽ ያለሺኝ
ያገሬ ልጅ ፍቅሬ እህቴ
ክፉ አይንካሽ እመቤቴ
የአይኔ ስስቴ
ያገሬ ልጅ ፍቅሬ እህቴ
ክፉ አይንካሽ እመቤቴ
የአይኔ ስስቴ
እንዴት እሆን ነበር
ከስደት ጋር ሆደ ባሻው እኔ
ምን ይውጠኝ ነበረ
በሰው ሀገር ባትኖሪ ከጎኔ
አልችለም ነበረ ብቻዬን ላድር
ጠቅልዬ ልኖር
እንዴት እሆን ነበር
ከስደት ጋር ሆደ ባሻው እኔ
ምን ይውጠኝ ነበረ
በሰው ሀገር ባትኖሪ ከጎኔ
አልችለም ነበረ ብቻዬን ላድር
ጠቅልዬ ልኖር
የሚስጥሬ ዋሻ
የሀገር ናፍቆት ህመም ብሶት ማስታገሻ
የእናት ሀገሬ ልጅ የእምባዬ ማበሻ
የሀዘኔ መርሻ
አንቺ ትብሽ እኔ እየተባባሉ እየረዳዱ
ህይወትን መጋራት ልብን ከፍቶ መስጠት
እንዲህ ነው ሲወዱ
እያፅናናሽ እያረጋጋሽኝ የምታረሳሺኝ
የትም የትም አንድ ነሽ ያለሺኝ
እያፅናናሽ እያረጋጋሽኝ የምታረሳሺኝ
የትም የትም አንድ ነሽ ያለሺኝ
እያፅናናሽ እያረጋጋሽኝ ይሄን ጉድ አስረሳሺኝ
የትም የትም አንድ ነሽ ያለሺኝ
እያፅናናሽ እያረጋጋሽኝ ይሄን ጉድ አስረሳሺኝ
የትም የትም አንድ ነሽ ያለሺኝ
ያገሬ ልጅ ፍቅሬ እህቴ
ክፉ አይንካሽ እመቤቴ
የአይኔ ስስቴ
ያገሬ ልጅ ፍቅሬ እህቴ
ክፉ አይንካሽ እመቤቴ
የአይኔ ስስቴ
ያገሬ ልጅ ፍቅሬ እህቴ
ክፉ አይንካሽ እመቤቴ
የአይኔ ስስቴ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя