Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Atamerm Woy текст песни

Исполнитель: Tsehaye Yohannes

альбом: Letinish


አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት
እዩዋት እዩዋት
የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት
በሏት በሏት
አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት
እዩዋት እዩዋት
የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት
በሏት በሏት
ያካሄዷን ውበት የአለባበሷን ወጓን አድንቁልኝ
የቆንጆዎች ቆንጆ እመቤት መሆኗን እወቁልኝ
ኦሆ ውበት ልብን ያሳሳል
ናፍቆቷን ልብን ያሳሳል
ኦሆሆ እዩልኝ አፈጣጠሯን
አሳሳቅ አነጋገሯን
ኦሆሆ የፍልሰታ ህብስት
አሀሀ የአጥብያ ንጋት መና
የተለየች ፍጡር
የአዳም ልጆች ብስራት
የመስቀል ደመራ
ኦሆ ችቦ ነደደባት
የእንቁጣጣሽ ጀንበር
የደረቷ ጥራት
ተረከዘ ሎሚ ገዳይ ባቷ
ኩሩ ዳሌ መቃ አንገቷ
ኦሆሆ
እንኮይ የመሰለው
ፀደይ ፊቷ
ሀሩ ፀጉሯ
ሙት አንጀቷ
በአለንጋ ጣቷ ጋሻ
ህይወት ዳግም አድሳ
የሰው ህግጋት ጥሳ
ታድናለች ፈውሳ
ፍቅር ነው መወደሷ
አጀብ ያሰኛል ለሷ
አጀብ ያሰኛል ለሷ
አጀብ አጀባ
አጀብ አጀባ
አጀብ አጀባ
አጀብ አጀብ
አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት
እዩዋት እዩዋት
የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት
በሏት በሏት
አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት
እዩዋት እዩዋት
የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት
በሏት በሏት
ታደገኝ ሰዐቱ
ጊዜ እና ዘመኑ ተለመነኝ
ለሊቱ ረጭ ይበል
ሳሞግሳት ልደር ደስ ይበለኝ
ኦሆ ውበት ልብን ያሳሳል
ናፍቆቷን ልብን ያሳሳል
ኦሆሆ እዩልኝ አፈጣጠሯን
አሳሳቅ አነጋገሯን
ሀረግ ነው ዛላዋ
ኦሆሆ ይጣራል ከርቀት
የቋንቋዋ ብስለት
አለው ልዩ ጥልቀት
ጨዋታ ጌጧ ነው
ኦሆሆ የለዛዋ ብቃት
የሚያቃልል ጭንቀት
ይሰጣታል ድምቀት
የሂሩት ምሳሌ መሽቆጥቆጧ
ያስጨንቃል ደግነቷ
ኦሆሆ
የኑሮ ፍሰሀ ቅንነቷ
ያዋልላል ጨዋነቷ ኦሆሆ
ሽንጧ በእውቅ የተሰራ
ኮከብ ጥሯሷ ሲያበራ
ፅልመት አስወጋጅ ጮራ
ወደ ፅድቅ የሚያመራ
ከንፈሯ እሸት ያፈራ
አቤት አይኗ ሲጣራ
አቤት አይኗ ሲጣራ
አቤት አቤታ
አቤት አቤቶ
አቤት አቤቷ
አቤት አቤቷ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители