Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Man Lebelsh текст песни

Исполнитель: Tsehaye Yohannes

альбом: Sakilgne


እንዳልጠይቅሽ ፍርቼ
እንግዳም አልሆንሽ ለአይኖቼ
በቅርብ የማዉቅሽ መሰለኝ
የት እንዳየሁሽ ግር አለኝ
እንዳልጠይቅሽ ፍርቼ
እንግዳም አልሆንሽ ለአይኖቼ
በቅርብ የማዉቅሽ መሰለኝ
የት እንዳየሁሽ ግር አለኝ
ተምታቶብኝ ላስታዉስ ብሞክር ትዝ አላለኝ
ሳብሰለስል ሁኔታዉ በሙሉ ግርም አለኝ
ዉብ ተፈጥሮ ማራኪ ደም ግባት አድሎሻል
ባላዉቅሽስ ቀርቤ ባደንቅሽ ምን ይልሻል
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ለአይኔ እንግዳ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ አልሆንሽብኝ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ የማዉቃት መሰልሽብኝ
ይልቅ ገጠመኝ ሆኖ ግር ብሎኛል መልክሽ
ለማስታወስ ሞክሪ ድንገት ከመጣሁልሽ
ለአፍታ ግርምታን ፈጥሮ አንዴ ለሆነዉ ነገር
ቀድሞ መግባባት እንጂ ምን ይጠቅምሻል ማፈር
እንዳልጠይቅሽ ፍርቼ
እንግዳም አልሆንሽ ለአይኖቼ
በቅርብ የማዉቅሽ መሰለኝ
የት እንዳየሁሽ ግር አለኝ
ለማናገር ታዲያ በምን መንገድ እችላለዉ
ባላዉቅሽም አዉቅሻለሁ እንጂ ምን እላዉ
የኔስ መቅረብ የማዉቃትን ቆንጆ በመምሰልሽ
በአጋጣሚዉ በይ እንተዋወቅ ማን ልበልሽ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ እኔ አልቻልኩም
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ችዬ ላልፍሽ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ የኔ ቆንጆ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ማን ልበልሽ
ጥፋት አለ ወይ ከእኔ ንገሪኝ ምን ጐደለ
በፈገግታ አነጋግሪኝ ባታዉቂኝስ ምን አለ
ደፊሬ ለማናገር ፈት ለፊትሽ ቆሚያለዉ
ካጠፋሁም ይቅርታ በኋላ እክስሻለዉ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ እኔ አልቻልኩም
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ችዬ ላልፍሽ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ የኔ ቆንጆ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ማን ልበልሽ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ እኔ አልቻልኩም
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ችዬ ላልፍሽ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ የኔ ቆንጆ
ማን ልበልሽና ምን ልበልሽ ማን ልበልሽ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители