ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ለመናገር መጎምጀቱ
ለኛስ ነው ወይ መድሃኒቱ
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ተጠራርተን ከየቤቱ
ቃልን መርጠን መሻማቱ
ሃምሳ ሎሚ ከብዶት ይሸከም ጉልበቴ
አታግዙኝ ይቅር ጌጤ ነው ቅርጫቴ
ለምን አደንቃለሁ ጥሩ ቃል መራጩን
በምላሱ ስለት የምናብ ቆራጩን
ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ
በተግባር መስካሪ እማኝ እንዳይጠፋ
አንድም ሳይጨበጥ ሳይዳሰስ ስንኳን
ጀግና ልንባል ነው ቃል እንዳሰካካን
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ተጠራርተን ከየቤቱ
ቃልን መርጠን መሻማቱ
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ለመናገር መጎምጀቱ
ለኛስ ነው ወይ መድሃኒቱ
አስተዋልኩኝ ብሎ ህመሜን ቢነግረኝ
አላጨበጭብም መድሃኒት ካልሰጠኝ
ለፈለፈው እንጂ መች አጣሁት እኔ
አይራቀቅብኝ እድናለሁ ያኔ
ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ
በተግባር መስካሪ እማኝ እንዳይጠፋ
አንድም ሳይጨበጥ ሳይዳሰስ ስንኳን
ጀግና ልንባል ነው ቃላት ካሰካካን
ሃምሳ ሎሚ ከብዶት ይሸከም ጉልበቴ
አታግዙኝ ይቅር ጌጤ ነው ቅርጫቴ
ለምን አደንቃለሁ ጥሩ ቃል መራጩን
በምላሱ ስለት የምናብ ቆራጩን
አስተዋልኩኝ ብሎ ህመሜን ቢነግረኝ
አላጨበጭብም መድሃኒት ካልሰጠኝ
ለፈለፈው እንጂ መች አጣሁት እኔ
አይራቀቅብኝ እድናለሁ ያኔ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя