Kishore Kumar Hits

Abinet Agonafir - Sew Ale текст песни

Исполнитель: Abinet Agonafir

альбом: Astaraky


ማነው ያለው አልልም አልጠይቅም፣
ማነው ያለው ብዬም አልጨነቅም፣
ማነው ያለው ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ፣
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ።
ማነው ያለው ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም፣
ማነው ያለው ውስጤን ላያውቀው ማንም፣
ማነው ያለው ስቆ ማለፍ መተው ነው፣
የሚያኖርም የሰራም ደግ አባት ነው።
አአአአአአይይይ
ለማን ብዬ ባዶነት ለሞላው፥
ለማን ብዬ ለገለባው ክብሬ፣
ለማን ብዬ ካበደው ጋር ልበድ፥
ለማን ብዬ ከጠፋው አብሬ፣
ለማን ብዬ እልህ ተጋብቼ፥
ጨካኝ ልሁን መራራቴን ትቼ።
ለማን ብዬ ባልተረጋገጠ፣
ለማን ብዬ መሬት ባረገጠ፣
ለማን ብዬ በደለበ ወሬ፣
ለማን ብዬ በወለደ በሬ፣
ለማን ብዬ ስጦታው ሰላሜን፣
ለማን ብዬ ልነጠቅ ደስታዬን።
ማነው ያለው ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ፣
ማነው ያለው ብልስ ማንን አምናለሁ፣
ማነው ያለው አውቀዋለሁ ባይ ብዙ፣
በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . .
እራስን ክቦ ለክብር ዝና፣
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና፣
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ፣
እንዴት ይገፋል ይሄ ተጨምሮ፣
ሰው ለቁርሱ እጁን አጣጥፎ፣
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ፣
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ቢዋል ሳታምን ግባ።
አአአአአአይይይ... ምምምም
ማነው ያለው አልልም አልጠይቅም፣
ማነው ያለው ብዬም አልጨነቅም፣
ማነው ያለው ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ፣
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ።
ማነው ያለው ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም፣
ማነው ያለው ውስጤን ላያውቀው ማንም፣
ማነው ያለው ስቆ ማለፍ መተው ነው፣
የሚያኖርህ የሰራም ደግ አባት ነው።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ .
ለማን ብዬ አለኝ ያሉት በምድር፣
ለማን ብዬ ፈጥኖ ለሚያሳፍር፣
ለማን ብዬ ከዘመኔ ስፍር፣
ለማን ብዬ ቅንጣት ለማልጨምር፣
ለማን ብዬ ወዳጅ ላፍራ ብዬ፣
የሰው ላድንቅ የኔን ቀን ገድዬ።
ለማን ብዬ ቃላት ከማይመርጠው፥
ለማን ብዬ ለከት ካጣ አንደበት፣
ለማን ብዬ ከማይጠቅም ምክር፥
ለማን ብዬ እርግማን ካለበት፣
ለማን ብዬ የኮኮብ ድምቀቴን፣
ለማን ብዬ ላጥፋው ማንነቴን።
ማነው ያለው ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ፣
ማነው ያለው ብልስ ማንን አምናለሁ፣
ማነው ያለው አውቀዋለሁ ባይ ብዙ፣
በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . .
እራስን ክቦ ለክብር ዝና፣
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና፣
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ፣
እንዴት ይገፋል ይህ ተጨምሮ፣
ሰው ለቁርሱ እጁን አጣጥፎ፣
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ፣
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ቢዋል ሳታምን ግባ።
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
አሉ ተባለን ሳታምን ግባ።
እ እ እ እ እህ እህ . .

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители