Hamelmal Abate - Keyanew текст песни
Исполнитель:
Hamelmal Abate
альбом: Sedet
ሲያዝንና ሲደሰት ሲያፈቅርም ከልቡ
ስሜቱን ይገልጻል በሞያ ጥበቡ
ሲያዝንና ሲደሰት ሲያፈቅርም ከልቡ
ስሜቱን ይገልጻል በሞያ ጥበቡ
♪
ሁሌም ለአዲስ ነገር ራሱን ያዘጋጀ
ጥበበኛ አይምሮ ጥበብ ያደራጀ
የህይወትን ዙሪያ ውስጡን ይዳሳል
ብዙ እንቅፋት አለው ይወድቃል ይነሳል
ውጥኑን ጀምሮት እስከሚጨርሰው
ልረፍን አያውቅም ከግብ እስኪያደርሰው
♪
የሙያ ድግሱን በመድርክ አቅርቦ
የታዳሚን መንፈስ አዝናንቶ መግቦ
የጥረቱን ዋጋ የድካም ውጤቱ
የህዝብ አድናቆት ነው የዘላለም ሀብቱ
የህዝቡ ፍቅር እንጂ ሀብትና ንብረቱ
ሌላ ምን ቅርስ አለው በቤት በማጀቱ
እውነታው ይሄው ነው የከያኒ ውበቱ
ሁል ግዜ ጠባቂ የወሩን መባቻ
ደርሶም ኪሱ አይሞላ ያው ጠብታ ብቻ
ሆዱን ለማሸነፍ ባይሸማቀቅም
የጎጆ ሽንቁር የጎጆ ሽንቁሩን ደፍኖበት አያውቅም
ላቡ ከፍሬው ጋር እስከሚሆን አቻ
ደስተኛነቱ ነው የሚስጥሩ መፍቻ
ላቡ ከፍሬው ጋር እስከሚሆን አቻ
ደስተኛነቱ ነው የሚስጥሩ መፍቻ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя