Hamelmal Abate - Dehna Hun текст песни
Исполнитель:
Hamelmal Abate
альбом: Yadelal
ደህና ሁን ቸር ይከተልህ
ዳግመኛ እስካገኝህ
ፈጣሪ በግራ ጎንህ
ጠባቂ ይሁንልህ
እያወኩ እንደምትመጣ እያመንኩ እንደማይህ
አልቻልኩም እምባ አሸነፈኝ እየሳኩ እንዳልሸኝህ
ልሂድ ካልከኝ የግድ ሆኖብህ ሳመኝ ሳመኝ ልሰናበትህ
♪
ጨርቅ ያርግልህና ይቅና መንገድህ
በሁድክበት ሁሉ ይብዛ ሰላምህ
ፍፁም እንዳይከፋህ ከጥኋት እስከ ማታ
ዉለህ እደርልኝ በሰላም በደስታ
በሃሳብ አንተን ተከትዬ
አብሬህ አድራለሁኝ ዉዬ
♪
አይምታህ ምንም እንቅፋት
ያርቅህ እሱ ከጥፋት
በፀሎት አስብሃለሁ
ለአፍታ መች እለይሀለሁ
አይምታህ ምንም እንቅፋት
ያርቅህ እሱ ከጥፋት
በፀሎት አስብሃለሁ
ለአፍታ መች እለይሀለሁ
♪
ደህና ሁን ቸር ይከተልህ
ዳግመኛ እስካገኝህ
ፈጣሪ በግራ ጎንህ
ጠባቂ ይሁንልህ
እያወኩ እንደምትመጣ እያመንኩ እንደማይህ
አልቻልኩም እምባ አሸነፈኝ እየሳኩ እንዳልሸኝህ
ልሂድ ካልከኝ የግድ ሆኖብህ ሳመኝ ሳመኝ ልሰናበትህ
♪
ከጎኔ ብርቅም ዛሬ ከጠገቤ
እስከመጨረሻዉ አትጠፋም ከልቤ
እስከምነገናኝ በአካል በአይነ ስጋ
ድምፅህ እንዳይርቀኝ እኔም እንዳልሰጋ
በሃሳብ አንተን ተከትዬ
አብሬህ አድራለሁኝ ዉዬ
♪
ሌት ተቀን አስብሃለዉ
በፅናት ጠብቅሀለዉ
አትርሳኝ አንተም አደራ
በመንፈስ ሁን ከኔ ጋራ
አይምታህ ምንም እንቅፋት
ያርቅህ እሱ ከጥፋት
በፀሎት አስብሃለሁ
ለአፍታ መች እለይሀለሁ
እወድሃለዉ
አፈቅርሃለዉ
ናልኝ በሰላም ጠብቅሀለዉ
እወድሃለዉ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя