Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Ewedhalehu текст песни

Исполнитель: Hamelmal Abate

альбом: Yadelal


መች ጠላሁህ ወድሃለሁ
እዉነት እዉነት እልሃለሁ
እንደኔ የሚወድህ በአለም ላይ ሰዉ አለ ወይ
እንደኔ የሚወድህ በአለም ላይ ሰዉ አለ ወይ
መች ጠላሁህ ወድሃለሁ
እዉነት እዉነት እልሃለሁ
እንደኔ የሚወድህ በአለም ላይ ሰዉ አለ ወይ
እንደኔ የሚወድህ በአለም ላይ ሰዉ አለ ወይ
ፍቅር በቃ ተከተተ
ብዬ ልቤን ሰጠሁ ለአንተ
በመዉደድህ ገዝተኸኛል
ከአንተ ወዲያ ምን ያምረኛል
እንደምወድህ ልብህ ያዉቀዋል
አንደበትህ ግን ይደብቀዋል
አታቃልብኝ ፍቅሬን ዋጋ
ሀሳቤ አንተ ነህ ሲመሽ ሲነጋ
አትወጂኝም አትበለኝ
ከአንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም የአንተዉ ነኝ
አትወጂኝም አትበለኝ
ከአንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም የአንተዉ ነኝ
እኔ ዛሬም ወድሃለሁ
ነገም ወድሃለሁ መች እጠላሃለሁ
እኔ ዛሬም ወድሃለሁ
ነገም ወድሃለሁ መች እጠላሃለሁ
(እወድሃለሁ)
(እወድሃለሁ)
(እወድሃለሁ)
(እወድሃለሁ)

መች ጠላሁህ ወድሃለሁ
እዉነት እዉነት እልሃለሁ
እንደኔ የሚወድህ በአለም ላይ ሰዉ አለ ወይ
እንደኔ የሚወድህ በአለም ላይ ሰዉ አለ ወይ
ከቤተሰብ ተነጥዬ ስለፍቅርህ ሁሉን ጥዬ
የአንተ ልሆን ወስኛለዉ ሌላ ለምን እመኛለዉ
ሁሉ ነገርህ ተመችቶኛል
ምን ጎደለብኝ ሁሉም ሞልቶኛል
አቋሜ ግልፅ ነዉ አይወላዉልም
እኔ ካለአንተ መኖር አልችልም
አትወጂኝም አትበለኝ
ከአንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም የአንተዉ ነኝ
አትወጂኝም አትበለኝ
ከአንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም የአንተዉ ነኝ
እኔ ዛሬም ወድሃለሁ
ነገም ወድሃለሁ መች እጠላሃለሁ
እኔ ዛሬም ወድሃለሁ
ነገም ወድሃለሁ መች እጠላሃለሁ
(እወድሃለሁ)
(እወድሃለሁ)
(እወድሃለሁ)
(እወድሃለሁ)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители