Hamelmal Abate - Yenie New текст песни
Исполнитель:
Hamelmal Abate
альбом: Yenie New
እድሌ እጣዬ ክፍሌ ባረኩት
በፍቅር የግሌ
እንዲሆን የውሃ አጣጬ
መረጥኩት ከሁሉ አብልጬ
እሱ ነው እድሌ እሱ ነው
ለኔ ሕይወት የተወሰነው
አይኖቼን እሱ ላይ ጥዬ
ከወንዶች መሃል ነጥዬ
እሱን ነው የወደድኩት
እሱን ነው ያፈቀርኩት
እሱን ነው በልቤ ላይ
እሱን ነው ያነገስኩት
♪
የኑሮዬ ጣፋጭ ቅመም
እርካታዬ እርካታዬ እርካታዬ
ከአዳም ልጆች የደረሰኝ የብቻዬ የብቻዬ ስጦታዬ
ለስጋ ለነፍሴ ሀሴት እንዲሆን የተሰጠኝ
ማንም ሰው የማይወስድብኝ
ማንም ሰው የማይነጥቀኝ
ተዉት ተዉት ተዉት ተዉት ተዉት
ላታገኙት አትመኙት
በቃ በቃ በቃ ልጁ የኔ ነው
የኔ ነው የኔ ነው
የሰጠሁት ልቤን ነው
ልቤን ነው ልቤን ነው
የወሰድኩት ልቡን ነው
ልቡን ነው ልቡን ነው
♪
የኔ የኔ የኔ የኔ የኔ የኔ
እድሌ እጣዬ ክፍሌ
ባረኩት በፍቅር የግሌ
እንዲሆን የውሃ አጣጬ
መረጥኩት ከሁሉ አብልጬ
እሱ ነው እድሌ እሱ ነው
ለኔ ሕይወት የተወሰነው
አይኖቼን እሱ ላይ ጥዬ
ከወንዶች መሃል ነጥዬ
ሁዋ ሁዋ ሀልባሂቡ
ሁዋ ሁዋ መሊፍ ቀልቢ
ሁዋ ሁዋ ሀልባሂቡ
ሁዋ ሁዋ መሊፍ ቀልቢ
♪
የናንተም የናንተ ነው የኔም የኔ የኔም የኔ
ቀልድ አላውቅም በዓይኔ አትምጡ በብሌኔ በብሌኔ
እንደ ሸት ባይታለፍም
እንደ ቀልድ አይቀጠፍም
ከኔ ነው አካል መንፈሱ
የማንም አይደለም እሱ
ተዉት ተዉት ተዉት ተዉት ተዉት
ላታገኙት አትመኙት
በቃ በቃ በቃ ልጁ የኔ ነው
የኔ ነው የኔ ነው
የሰጠሁት ልቤን ነው
ልቤን ነው ልቤን ነው
የወሰድኩት ልቡን ነው
ልቡን ነው ልቡን ነው
ኢነተሃ ቲያቲ ረቢ
ኢንተሳ አደቲ ጂዝሚ
ኢንተባ አጀቲ ነበሲ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя