Kishore Kumar Hits

Dawit Cherent - Fiteh - live текст песни

Исполнитель: Dawit Cherent

альбом: In Pursuit of ...


ለካ በወይኒ ቤት ይኖራል ፃድቅ ሰው
ግፍ ያላረገ ሀሰት የከሰሰው
ለካ ቤተ መቅደስ ይኖራል ወንበዴ
የሰው ልጆች ፍትህ እንዲ ነው አንዳንዴ
ምን አይነት አለም ነው ፍትህ ያጏደለ
ጉቦኛ ለሆነ ፍርዱ ያጋደለ
እውነት ካልፈረደ በስተመጨረሻ
ድንጋይ አያደቅም የፍትህ መዶሻ
መሰሶ ያቆሙ ጉድፍ ያነፃሉ
ለነሱ ነፃነት ሌላ ይከሳሉ
በሀሰት አትፍረድ ቢሆንም ነገሩ
አሁንም ግን አሉ በመርዝ የሚሰክሩ
ምን አይነት አለም ነው ፍትህ ያጏደለ
ጉቦኛ ለሆነ ፍርዱ ያጋደለ
እውነት ካልፈረደ በስተመጨረሻ
ድንጋይ አያደቅም የፍትህ መዶሻ
የዘሩትን ማጨድ ስለተወሰነ
በምድር ህግጋት ስለተበየነ
ሸሽቶ አያመልጥም የህሊና እስረኛ
መፍረዱ አይቀርም እውነት ያለዳኛ
ምን አይነት አለም ነው ፍትህ ያጏደለ
ጉቦኛ ለሆነ ፍርዱ ያጋደለ
እውነት ካልፈረደ በስተመጨረሻ
ድንጋይ አያደቅም የፍትህ መዶሻ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Sew-EP

2019 · Мини-альбом

Humble

2019 · Мини-альбом

Похожие исполнители

Tsedi

Исполнитель