Kishore Kumar Hits

Selam Desta - Fitsum Alaferem текст песни

Исполнитель: Selam Desta

альбом: Alderaderem


ስለበደላችን ደቀቀ
ስለኃጥያታችን ቆሰለ
ስለመተላለፋችን ሞተ
በመገረፉ ቁስል ፈወሰን
ስለበደላችን ደቀቀ
ስለኃጥያታችን ቆሰለ
ስለመተላለፋችን ሞተ
በመገረፉ ቁስል ፈወሰን

በቀራኒዮው ስፍራ በመስቀል የሞተው
በእሾህ ሲጎነጉኑ ደሙ የፈሰሰው
በጦር ጎኑን ሲሉ በአለንጋ ሲልጡ
ዝም ማለቱ ለእኛ ነው መራራን ሲያጠጡ
ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም
ስሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር
ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም
ስሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር

በእራስ ቅሉ መንደር የፈሰሰው ደሙ ንጹህ ነው
ያለዋኖስ ያለበጐች ደም የአለምን በደል ጠረገው
ደሙን ይዞ ገባ ወደ አባቱ አወረደ ከላይ ምሕረቱን
አመጻችን ሁሉ ተወግዶ ተቆጠረ በእኛ ላይ ፅድቁ
ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም
ሥሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር

እጅጉን በችንካር አጥብቀው ወጠሩ
ጀርባውን በጅራፍ እያቆሰሉ
የአለማት ፈጣሪን ያለእፍረት ቢንቁ
ጸሀይ እና ጨረቃ እርሱን አከበሩ
እጅጉን በችንካር አጥብቀው ወጠሩ
ጀርባውን በጅራፍ እያቆሰሉ
የአለማት ፈጣሪን ያለእፍረት ቢንቁ
ጸሀይ☀️ እና ጨረቃ ጌታን አከበሩ
በምሕረቱ ነው ባለጠጋ
እኛን ሊምር ወደደ ጌታ
በምሕረቱ ነው ባለጠጋ
እኔን ሊምር ወደደ ጌታ
እኛን አለ ሩሃማ
እኛን አለ ሩሃማ
እኔን አለ ሩሃማ
እኔን አለ ሩሃማ
ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም
ሥሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители