Kishore Kumar Hits

Endalkachew Hawaz - Amlake Metamegnaye New текст песни

Исполнитель: Endalkachew Hawaz

альбом: Egziabher Tilik New


አዝ፦ አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)
በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ እኖራለው
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፣ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
የሌሊቱን ፡ ግርማ ፡ መቼ ፡ እፈራለሁ (፪x)
እውነት ፡ እንደጋሻ ፡ ዙሪያዬን ፡ ከቦኛል
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ይመራኛል
አዝ፦ አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)
በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ እኖራለው
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፣ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሆኖ
ማዳኑን ፡ አሳየኝ ፡ ምህረቱን ፡ አግንኖ (፪x)
በጠራሁት ፡ ጊዜ ፡ ፈጥኖ ፡ መለሰልኝ
እንዳልሰናከል ፡ በእጆቹ ፡ አነሳኝ (፪x)
አዝ፦ አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)
በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ እኖራለው
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители