እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ይህን ብቻ
እርሱ እንደሆነ የሁሉ ነገር መርቻ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው በምድር በሰማይ
ሁሉን ማድረግ የሚችል የለም ከእርሱ በላይ
በሰራዊት ብዛት አይድንም ንጉሱ
ጦረኛው ከሸሸ አይረዳው ፈረሱ
ዘየድኩኝ ለእራሴ እኔ ግን እንደቃሉ
ልቤን በእርሱ ጥዬ በእግዚአብሔር በኃያሉ
ኃይል ሁሉ የእርሱ ነው ብርታት ሆነ ጉልበት
የሰማይ ምሰሶ እጁ የፍጥረታት መሠረት
በክንዱ ተደግፌአለሁ
ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
በክንዱ ተደግፌአለሁ
ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
አሀ የእግዚአብሔር ነው
አሀ ኃይል የእግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ይህን ብቻ
እርሱ እንደሆነ የሁሉ ነገር መርቻ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው በምድር በሰማይ
ሁሉን ማድረግ የሚችል የለም ከእርሱ በላይ
ኃያላንን ፈጥሮ ኃይሉን የገለጠ
አስቦ በቃሉ ፍጥረት የቀረጸ
የሰማይ ሥርዓት የምድር ኃይል ጥግ
ሁሉ ተዳደረ በደነገገው ህግ
ኃይል ሁሉ የእርሱ ነው ብርታት ሆነ ጉልበት
የሰማይ ምሰሶ እጁ የፍጥረታት መሠረት
በክንዱ ተደግፌአለሁ
ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
በክንዱ ተደግፌአለሁ
ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
አሀ የእግዚአብሔር ነው
አሀ ኃይል የእግዚአብሔር ነው
አሀሀ ይህንን እውነት ተረድቼ አይቼ
አሀሀ አልሸበርም ሌላውን ሰግቼ
አሀሀ የያዝኩት ብርቱ ኃያሉ ጌታዬ
አሀሀ እግዚአብሔር ነው ኃይሌ መመኪያዬ
አሀሀ ይህንን እውነት ተረድቼ አይቼ
አሀሀ አልሸበርም ሌላውን ሰግቼ
አሀሀ የያዝኩት ብርቱ ኃያሉ ጌታዬ
አሀሀ እግዚአብሔር ነው ኃይሌ መመኪያዬ
በክንዱ ተደግፌአለሁ
ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
በክንዱ ተደግፌአለሁ
ከለላ ሆኖልኝ አለሁ
በምንም እንዳልሰጋ
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
አሀ የእግዚአብሔር ነው
አሀ ኃይል የእግዚአብሔር ነው
አሀ ኃይል የእግዚአብሔር ነው
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя