ህርወትክን ሰጠህ የገለጥክልኝ
የመስቀል ፍቅርህ
በውስጤ ፅልመት ብርሃን ፈንጥቋል
እኔን መውደድህ ሌላ መሰለኝ
የፍቅርን ትርጉም ፍቺው ነህ አንተ
ፍቅርን ያሳየህ
ሞትለተገባው አራስህን ሰጠህ
እራስህን ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር
አላውቅም እኔ እንዲሁ መውደድ
ከክብሩ ወርዶ ሆነ መስዋእት
ደዌን ተሸከምክ (ደዌን ተሸከምክ)
ስለኔ ታመምክ
በፍቅርህ ስፋት (ስፋት ፣ ብዛት)
ያን ሁሉ ስቃይ ችለህ ተቀበልክ
ነፍሴን አዳንካት
በበደልኩት በደል ፍርድ ሲገባኝ
ለሃጢአቴ ዋጋ
ፍቅር ግድ ብሎህ
እኔን ተክተህ
አንተ ተወጋህ
ያለ ምክንያት የሚያፈቅር
ሰው አላውቅም እንዲሁ የሚል
ሁሉም ሲወድ ምላሽ ያያል
ካልመሰለውም ይለያያል
ያንተስ መውደድ ሁሌ ይኖራል
ብርቅ እንኳን ያቀርበኛል
ያቀርበኛል
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя