ተስፋ በራቀበት እረፍት በሌለበት
ሙት በነገሰበት
መኖር ልማድ ሆኖ መዋል ማደር
በከንቱ ምኞት ጥላ ስር
የነፍሴን መጨነቅ ውትረት ተመልክተህ
በቃልህ ብርሃን ደርሰህ በመንፈስህ
በድኑን መንፈሴን አንተ ቀሰቀስህ
እንዴት የሚገድም ነው የሚደንቅ ነገር
ነፍስን ላንተ ሰጦ በእረፍት መኖር
ክብር ይሁን ላንተ ክብር ሃሌሉያ
መረጠህ አደረከኝ የክብርህ ማደሪያ
የነፍሴን መጨነቅ ውጥረት ተመልክተህ
በቃልህ ብርሃን ደርሰህ በመንፈስ
በድኑን መንፈሴን አንተ ቀሰቀስህ
እንዴት የሚገድም ነው የሚደንቅ ነገር
ነፍስን ላንተ ሰጦ በእረፍት መኖር
ክብር ይሁን ላንተ ክብር ሃሌሉያ
መረጠህ አደረከኝ የክብርህ ማደሪያ
ያንተ ናት ነፍሴ እኔነቴ
ማደሪያህ ነው የውስጥ ውስጠቴ
ቀድሻለሁ ላንተ ህይወቴን
ያንተ ናት ነፍሴ እኔነቴ
ማደሪያህ ነው የውስጥ ውስጠቴ
ቀድሻለሁ ላንተ ህይወቴን
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя