Kishore Kumar Hits

Feven Yoseph - Wudasse текст песни

Исполнитель: Feven Yoseph

альбом: Chanting Soul


ጌታዬ ላወድስህ ስል
ለምን ይሆን ሚጠፋኝ ቃል
እስቲ አፍስሰው መንፈስህን
መግለጽ ብችል የገባኝን
ጌታዬ ላወድስህ ስል
ለምን ይሆን ሚጠፋኝ ቃል
እስቲ አፍስሰው መንፈስህን
መግለጽ ብችል የገባኝን
ክብርህ እጅግ ገንኖ
በምድር በሰማይ
ተደምሜ እያየሁ
የጥበብህን ሃይል
ፈልጌ ላወራው
በቅኔ በዜማ
ግርማህን ለመግለጥ አነሰብኝ ቋንቋ
አልበቃኝም ቋንቋ
ኦ ውዳሴ ግርማዊ ለሆንከው
ለተዋበው ማንነትህ
ይሁን ይሁን ይኸው ተቀበለው
ኦ ውዳሴ ግርማዊ ለሆንከው
ለተዋበው ማንነትህ
ይሁን ይሁን ይኸው ተቀበለው

እንዲህ ያለ ጥበብ
ሕዋውን ያፀና
ቃላት የማይገልፁት
የሆነ ገናና
ምናለ ቢኖረኝ
ከዚህ ሌላ ልሳን
እንድቆም ማሕሌት ለታላቁ ግርማ
ኦ ኦ ግርማ
ኦ ውዳሴ ግርማዊ ለሆንከው
ለተዋበው ማንነትህ
ይሁን ይሁን ይኸው ተቀበለው
ኦ ውዳሴ ግርማዊ ለሆንከው
ለተዋበው ማንነትህ
ይሁን ይሁን ይኸው ተቀበለው
ኦ ውዳሴ ግርማዊ ለሆንከው
ለተዋበው ማንነትህ
ይሁን ይሁን ይኸው ተቀበለው
ኦ ውዳሴ
ኦ ውዳሴ
ኦ ውዳሴ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители