ሚስጢሬን ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ የምነግርህ
የውስጤን ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ የምነግርህ
እገዛህ ፡ ያሻኛል ፡ ማጽናናትህ (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ነሃ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ነሃ
የእኔ ፡ ነሃ ፡ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነሃ (፪x)
ጨለማው ፡ ሲቀርብ ፡ የብርሃንህን ፡ ወጋገን ፡ ስሻ
ሕይወቴን ፡ ከቦ ፡ የዓመጻ ፡ ልጅ ፡ ሳጣ ፡ መሸሻ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ አጽናኝ ፡ አስተማሪ
ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ሲሄድ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ቀሪ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ነሃ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ነሃ
የእኔ ፡ ነሃ ፡ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነሃ (፪x)
የመማጸኛ ፡ ከተማዬ ፡ ነህ ፡ ነህ ፡ ነህ
ነፍሴ ፡ ከአዳኝ ፡ ምታመልጥብህ
ምህረት ፡ ማገኛዬ ፡ ነህ ፡ ምህረት
ቸርነት ፡ ማገኛዬ ፡ ነህ ፡ ቸርነት
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከመከራዬ ፡ አድነኝ ፡ ሁንልኝ ፡ ኃይሌ
የኃይሌ ፡ ትምክት ፡ አንተ ፡ ነህ
ሁሌ ፡ ላምልክህ ፡ በሕይወት ፡ ምሥጋና
በሕይወት ፡ ምሥጋና (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя