Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Merto Mafqer Yelm текст песни

Исполнитель: Girma Tefera Kassa

альбом: Gin Yet Hager


አይኔ
ድንገት ሰርቆ አይንሽን ያየውና
ሰው ያስታውሰኛል እንደገና
ልቤ
ካዳፈንኩት እሳት እየጫረ
ከገፅሽ ያነባት ጀማመረ
እኔስ ምዬ ነበር ላላነሳት
ምስሏን ባንቺ ገልፃው እንዴት ልርሳት
የረሳኋት መስሎኝ አንቺን በማግኘቴ
በድንገት ወደ'ሷ ይጓዛል ስሜቴ
ልሰጥሽ ወስኜ ልቤን ሳሰናዳ
የሷን ምስል አየሁት ከገፅሽ ሰሌዳ
በመልካምነትሽ ልተውሽ ባልወድም
ልለይሽ የኔ አለም ጉዳትሽን አልፈቅድም
መርጠው ባልመጡበት በእንግድነት አለም
አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም
አሄሄሄሄሄ አልረሳትም
ኦሆሆሆሆ አልረሳትም
አይኔ
ድንገት ሰርቆ አይንሽን ያየውና
ሰው ያስታውሰኛል እንደገና
ልቤ
አበቃ አከተመ ካለ ኋላ
ስንቴ አመሳሰላት ካንቺ ገላ
እኔስ ምዬ ነበረ ላላነሳት
ምስሏን ባንቺ ገልፃው እንዴት ልርሳት
ትርፍ የታለ ውዴ ብሰጥሽ ራሴን
የራቀን ፍለጋ ካባከንኳት ነብሴን
ልካስሽ ባልልም ለዋልሽው ውለታ
ይቅርታ ከልቤ ለነፈግኩሽ ደስታ
በመልካምነትሽ ልተውሽ ባልወድም
ልለይሽ የኔ አለም ጉዳትሽን አልፈቅድም
መርጠው ባልመጡበት በእንግድነት አለም
አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም
አሄሄሄሄሄ አልረሳትም
ኦሆሆሆሆ አልረሳትም

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители