Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Liyu Neger текст песни

Исполнитель: Girma Tefera Kassa

альбом: Gin Yet Hager


ከውብ ቃል ከመልክም በላይ
ለጉድ ነው ያደለሽ ፀባይ
ካ'መልሽ ጠልቆ ሚሰገር
አለሽ አለሽ አለሽ ብዙ ልዩ ነገር
አለሽ አለሽ አለሽ ብዙ ልዩ ነገር
ከውብ ቃል ከመልክም በላይ
ለጉድ ነው ያደለሽ ፀባይ
ካ'መልሽ ጠልቆ ሚሰገር
አለሽ አለሽ አለሽ ብዙ ልዩ ነገር
አለሽ አለሽ አለሽ ብዙ ልዩ ነገር
አካልሽ ሳያንሰው የመወደድ ለዛ
የመጣፈጥ የመወደድ ለዛ
አንደበትሽ ሲሆን ቀልብን የሚገዛ
ውሎ እያደር ቀልብን የሚገዛ
ከሚታየው በላይ ከታደለሽ ውበት
ከተቸረሽ ከታደለሽ ውበት
ሚዛኑን ይደፋል የፀባይሽ ጉልበት
የማስተዋል የፀባይሽ ጉልበት
አመል ገንኖ ቢወዳደር ቢታይ ባ'ገር
የት ይገኛል ማን እንዳንቺ ልዩ ነገር
ልዩነትሽን አውጃለሁ ባ'ደባባይ
ፍቅር ቃኝቶ እርቅ ያወርዳል ያንቺ ፀባይ
አለሽ ብዙ (ልዩ ነገር)
የሚወራ (ልዩ ነገር)
ከፀባይሽ (ልዩ ነገር)
ያልተወራ (ልዩ ነገር)
አለሽ ብዙ (ልዩ ነገር)
የሚነገር (ልዩ ነገር)
ከፀባይሽ (ልዩ ነገር)
የሚሰገር (ልዩ ነገር)
የሚሰገር የሚሰገር
ከፀባይሽ የሚሰገር
የሚሰገር የሚሰገር
ከፀባይሽ የሚሰገር
ከውብ ቃል ከመልክም በላይ
ለጉድ ነው ያደለሽ ፀባይ
ካ'መልሽ ጠልቆ ሚሰገር
አለሽ አለሽ አለሽ ብዙ ልዩ ነገር
አለሽ አለሽ አለሽ ብዙ ልዩ ነገር
በማይነጥፈው ፍቅር በማይጎድለው እመነት
ከቃልኪዳን ባልጎደለው እምነት
እንደታሰረ አንጀት በእህት በእናትነት
እንደኖረው በእህት በእናትነት
መውደድሽ ሲገባው ልቤን እየቆየ
ሲያበረታው ልቤን እየቆየ
የሴትነት ክብሩ በፀባይሽ ታየ
ገኖ ለዛው በፀባይሽ ታየ
አመል ገንኖ ቢወዳደር ቢታይ ባ'ገር
የት ይገኛል ማን እንዳንቺ ልዩ ነገር
ልዩነትሽን አውጃለሁ ባ'ደባባይ
ፍቅር ቃኝቶ እርቅ ያወርዳል ያንቺ ፀባይ
አለሽ ብዙ (ልዩ ነገር)
የሚወራ (ልዩ ነገር)
ከፀባይሽ (ልዩ ነገር)
ያልተወራ (ልዩ ነገር)
አለሽ ብዙ (ልዩ ነገር)
የሚነገር (ልዩ ነገር)
ከፀባይሽ (ልዩ ነገር)
የሚሰገር (ልዩ ነገር)
የሚሰገር የሚሰገር
ከፀባይሽ የሚሰገር
የሚሰገር የሚሰገር
ከፀባይሽ የሚሰገር

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители