ብቻዬን ቁጭ ብዬ አዝኜ በቤቴ
በጣም እያመመኝ የውስጥ ስብራቴ
በድንገት ኢየሱስ ደረሰልኝ
ሰባራውን ጠጋኝ እውነተኛ ዳኛ
እውነተኛ ዳኛ
የደካሞች አሳራፊ
ኢየሱስ አለ ነፍሴ እረፊ
ሸክም ከብዶበት የሚንገላታ
ወደዚህ ጌታ መጥቶ ይበርታ
ዓይኔን አንስቼ ከሰው ላይ
ሀዘኔን ረሳሁ ኢየሱስን ሳይ
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
የፈተና መዓት በላዬ ቢፈስ
ጸሎቴ በሙሉ ባይመለስ
ዝቅ ዝቅ እላለው ሌላ አያምረኝም
ቤዛዬን ኢየሱስ በፍፁም አልክድም
በፍፁም አልክድም
ጌታዬ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ኢየሱስ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ኃጢያተኛ ሳለሁ ሰዎች ሲገፉኝ
የናዝሬቱ ኢየሱስ አይቶ ራራልኝ
እንደ ኃጢያቴ ያልፈረደብኝ
የእግዚአብሔር ልጅ እሱ ለእኔ አዘነልኝ
ለእኔ አዘነልኝ
ጌታዬ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ኢየሱስ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
የደካሞች አሳራፊ
ኢየሱስ አለ ነፍሴ እረፊ
ሸክም ከብዶበት የሚንገላታ
ወደዚህ ጌታ መጥቶ ይበርታ
ዓይኔን አንስቼ ከሰው ላይ
ሀዘኔን ረሳሁ ኢየሱስን ሳይ
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя