በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ
♪
ይበላል ትግስቱ ያላለቀ
♪
ጌታውን የጠበቀ ሰው
ስፍሪዬን አለቅም ያለው
እሱ ሰው ከበረ አሄ
ጌታን ያከበረ
እሱ ሰው ከበረ አሄ
ጌታን ያከበረ
♪
ስሞዖን ትጉህ ሰው ፃድቅ ሰው ነበረ
አያለው ቅዱሱን እያለ የኖረ
ሲጠብቅ ቆይቶ ህፃኑን ሲያየው
እጆቹን አንስቶ እንደዚህ አለው
ለህዝቦች ሁሉ መድኃኒት መድኃኒት
የሆነውን እሱን ስላየሁት ስላየሁት
መኖር አልሻም ውሰደኝ በቃ ውሰደኝ በቃ
በፅድቅ የኖርኩት እሱን ጥበቃ ጌታን ጥበቃ
ለኔ ስኬት ለኔ ስኬት
ለኔ ስኬት ልጁን ማየት
ለኔ ከፍታ ለኔ ከፍታ
ለኔ ከፍታ ፊትህ ነው ጌታ
♪
ያርስ የለ ወይ በበጋ ልቡን ጥሎ
ገበሬው አምኖ ይዘንባል ብሎ
በደረቅ መሬት አምኖ ያረሰ
በክረምት እርሻው እረሰረሰ
እኔው እጠብቅሃለው
መውደዴን በዚ አሳይሃለው
አንድ ቀን ዓለም እያየህ
ልትወስደኝ ትመጣልኛለህ
እስክትመጣ እስክትመለስ
እጠብቅሃለው ውዴ ኢየሱስ
ጠነከረብኝ ፍቅርህ በረታ
በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ
በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ
ይበላል ትግስቱ ያላለቀ
♪
ጌታውን የጠበቀ ሰው
ስፍሪዬን አለቅም ያለው
እሱ ሰው ከበረ አሄ
ጌታን ያከበረ
እሱ ሰው ከበረ አሄ
ጌታን ያከበረ
♪
ፍጻሜው ክብር ነው አንተን መጠበቄ
መብራቴን አብርቼ ወገቤን ታጥቄ
እጠብቅሃለው እስክትመለስ
ሙሽራው አዳኜ ጌታዬ ኢየሱስ
ፊትህን እንዳይ ተርቤ የለ ወይ እርቦኝ የለ ወይ
ለጥቂቶች መዳን ብትዘገይ ብትዘገይ
ጨመረብኝ ፍቅርህ በየዕለቱ በየዕለቱ
ተናፍቀሃል ኢየሱስ የናዝሬቱ የናዝሬቱ
እስክትመጣ እስክትመለስ
እጠብቅሃለው ውዴ ኢየሱስ
ጠነከረብኝ ፍቅርህ በረታ
በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя