Kishore Kumar Hits

Bereket Tesfaye - Lemelkam Honeling текст песни

Исполнитель: Bereket Tesfaye

альбом: Memihiru


ለካ ይታለፋል ማይታለፈው
ከልኩ አያልፍም የሰው ፈተናው
ምጠፋ መስሎኝ ፈራች እንጂ ነፍሴ
ለካ ያስጨነከኝ ለጥቅሜ ለራሴ
በእሳት እያለፍኩ ስፈተን
ወርቅ አደረገው ህይወቴን
በእሳት እያለፍኩ ስፈተን
ወርቅ አደረገው ህይወቴን
ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ
አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ
ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ
አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ
ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ
እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር ዕቃ
ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ
ልቤን አጀገነው ቅዱሱ መንፈስ
ቀዝቃዛ ህይወቴ በፈተናው ሞቀ
እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ
ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ
መቼ መሰለኝ የምሰራ
ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ
እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ
(ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ)
(ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ)
(ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ)
(ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ)
ሆነልኝ ሆነልኝ (ለመልካም)
ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለመልካም)
ሆነልኝ ሆነልኝ (ለበጎ)
ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለበጎ)
በመከራ ውስጥ መታዘዝን ተማረ
በስጋው ወራት አንተን አከበረ
እኛ ዳንን እንጂ በእርሱ መከራ
ህይወታችን ጣፍጧል በጠጣው መራራ
እሱ ኃያል ሳለ ምስኪን መሰለ
ከአመፀኞች ጋር ተሰቀለ
በጌታ መከራ ስንቶች ዳኑ
አቀረባቸው ወደ ዙፋኑ
ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ
አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ
ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ
አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ
ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ
እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር ዕቃ
ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ
ልቤን አጀገነው የጌታ መንፈስ
ቀዝቃዛ ህይወቴ በፈተናው ሞቀ
እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ
ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ
መቼ መሰለኝ የምሰራ
ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ
እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ
(ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ)
(ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ)
(ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ)
(ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ)
ሆነልኝ ሆነልኝ (ለመልካም)
ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለመልካም)
ሆነልኝ ሆነልኝ (ለበጎ)
ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለበጎ)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Live

2018 · альбом

Похожие исполнители