የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
የሰው ዘር ሁሉ ያዳም ስህተት
ይዞት ወደቀ ወደ ጥፋት ወደ ጥፋት
ማንም እንዳይድን ይሄን ቢረዳ
ሊከፍለው መጣ ለኃጢያት ዕዳ አወይ ለእኔ ዕዳ
የኃጢያት ደሞዝ ነውና ሞት
ሞቴን ሞተልኝ ሰጠኝ ሂወት ሰጠኝ ሂወት
ኃጢያት ተሻረ ከእኔ ላይ
በፈሰሰልኝ ጎልጎታ ላይ ቀራኒዮ ላይ
በገዛ ደሙ እርቅ አወረደ
የጠፋሁትን ስለወደደ
ኃጥዕ ተብዬ ስም ለወጣልኝ
በደሙ አንፅቶ ፃድቅ አስባለኝ
ከደጉ አባቴ አሁን ታረቅኩ
በቅዱስ ደሙ ስለታጠብኩ
ሌላ አማላጅ ሳያስፈልገኝ
በቀኙ ሆንኩ ደሙ አቀረበኝ
የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ፀሎት ነው የሚያስታርቀኝ
የኢየሱስ ደም ያላነፃኝ
የማን ፀሎት ነው የሚያነፃኝ
የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ምልጃ ነው የሚያስታርቀኝ
የኢየሱስ ደም ያላጠበኝ
የማን ምልጃ ነው የሚያጥበኝ
ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ
ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ
ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ
ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ
የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
ለሆንኩት ለኔ ለሞት ፍርደኛ
በአብ ቀኛ ያለ አንዱ ብቸኛ
ስለበደሌ እሱ ነው ዋሴ
የሚቆምልኝ ልክ እንደ ራሴ
መሰላል ያየው ያዕቆብ በህልሙ
መካከለኛ ነው ክቡር ደሙ
ሰማይ ከእኔ ጋር ዕርቅ ያደረገው
በማንም አይደል በኢየሱስ ደም ነው
ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ
ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ
ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ
ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ
የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው ዛሬም ትኩስ ነው አማላጄ ነው
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя