መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ
ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ
መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል
ይወደኛል ፡
ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል
ነፍሱን ፡ የሰጠው ፡ ስለእኔ ፡ የታደገኝ ፡ ከኩነኔ
ምህረቱን ፡ ያበዛልኝ ፡ ይቆመልኝም ፡ ከጐኔ
ነፍሴ ፡ ታምናው ፡ ረክታለች ፡ በጸጋው ፡ ብዛት ፡ ቆማለች
ያንን ፡ አስፈሪ ፡ ጨለማ ፡ ከአምላኳ ፡ ጋር: ተሻግራለች
ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ሲሰቃይ ፡ እንደሚወደኝ ፡ ገብቶኛል
ሞት ፡ ቢመጣ ፡ በመከራ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይመቸኛል
ይመቸኛል
መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ
ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ
መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል
ይወደኛል ፡
ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል
የፍቅሩ ፡ ጥልልቀት ፡ ሲገባኝ ፡ ልቤን ፡ ሰጠሁ ፡ እንዲገዛኝ
ይንገሥብኝ ፡ ወድጃለሁ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ
ዋላ ፡ ውሃዋን ፡ እንደምትሻ ፡ እኔን ፡ ዘወትር ፡ እጠማዋለሁ
በነፍሴ ፡ ወደማደሪያው ፡ ወደ ፡ ፡ እርሱ ፡ እገሰግሳለሁ
የሚለየኝ ፡ ማነው ፡ ከእርሱ ፡ በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ አስሮኛል
ሞት ፡ ቢመጣ ፡ በመከራ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይመቸኛል
ይመቸኛል
መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ
ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ
መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል
ይወደኛል
ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя