Kishore Kumar Hits

Yohannes Girma - Yelebie Desta текст песни

Исполнитель: Yohannes Girma

альбом: Erste Neh, Vol. 2


አዝ፦ የልቤ ፡ ደስታ ፡ ጌታ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ የሱስ
በገናዬን ፡ ልያዝ ፡ ልቀኝልህ
ነፍሴ ፡ ውላ ፡ ታድራለች ፡ በስምህ (፪x)
ምንም ፡ በሌለበት ፡ ማይነጥፍ ፡ ደስታ
ብር ፡ ያልደጋገፈው ፡ የዚህ ፡ አለም ፡ ስጦታ
ፊትን ፡ የሚያበራ ፡ ከላይ ፡ የሆነው
ዘላቂው ፡ ደስታዬ ፡ ጌታ ፡ ባንተ ፡ እኮ ፡ ነው
አዝ፦ የልቤ ፡ ደስታ ፡ ጌታ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ የሱስ
በገናዬን ፡ ልያዝ ፡ ልቀኝልህ
ነፍሴ ፡ ውላ ፡ ታድራለች ፡ በስምህ (፪x)
አይኖቼን ፡ ወደ ፡ ተራሮች ፡ ባነሳ
መመኪያን ፡ ለማግኘት ፡ ለእኔ ፡ የሚሳሳ
ለአይን ፡ የሚሞላ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ አላየሁ
ይልቅ ፡ ባንተ ፡ ሆነ ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ የሚለው
አዝ፦ የልቤ ፡ ደስታ ፡ ጌታ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ የሱስ
በገናዬን ፡ ልያዝ ፡ ልቀኝልህ
ነፍሴ ፡ ውላ ፡ ታድራለች ፡ በስምህ (፪x)
በስደት ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ በደረቅ ፡ በረሃ
ለአይን ፡ ተስፋ ፡ ሳይኖር ፡ ለጥም ፡ የሚሆን ፡ ውሃ
ዙሪያ ፡ ሲጨላልም ፡ መጽናናት ፡ ሲሳነኝ
በእንግድነት ፡ ሀገር ፡ ስራህ ፡ መዝሙር ፡ ሆነኝ
አዝ፦ የልቤ ፡ ደስታ ፡ ጌታ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ የሱስ
በገናዬን ፡ ልያዝ ፡ ልቀኝልህ
ነፍሴ ፡ ውላ ፡ ታድራለች ፡ በስምህ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители