ስትወድ ፡ ብዙ ፡ ስትምር ፡ ብዙ
ደግነትህ ፡ አበዛዙ
መልካምነትህን ፡ ለእኔ ፡ አልቆጠብከው
ለያንዳንዱ ፡ ነገር ፡ አብዝተህ ፡ አየሁ
ከለመንኩህ ፡ እና ፡ ካሰብኩት ፡ በላይ
ሁሉ ፡ ተከናውኖ ፡ ተደርጎልኝ ፡ ሳይ
ምለውን ፡ አጣሁ ፡ ዝም ፡ አሰኘኝ
የአንት ፡ ስራ ፡ አስደነቀኝ (፪x)
አዝ፦ ከተደረግልኝ ፡ በጎነት ፡ አንዳችም ፡ ለእኔ ፡ ማይገባ ፡ ነበር
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ አርገሃልና ፡ እደነቃለሁ
አብዝቼ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x)
ኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ አይደል ፡ ብዙ
ብልጠት ፡ በዝቶ ፡ አልደርስኩ
ለእኔ ፡ አንተ ፡ በርትተህ ፡ ተናጥቀህልኛል
በርትተህ ፡ ተውግተህ ፡ ምርኮን ፡ በዝብዘሃል
እንካ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ላንት ፡ ላብዛ ፡ ላብዛ
ሳልጠግብ ፡ ውዳሴህም ፡ አፌን ፡ ከቶ ፡ አልዝጋ
ወዳጄ ፡ ነህ ፡ የምወድህ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ የማበልጥህ (፪x)
አዝ፦ ከተደረግልኝ ፡ በጎነት ፡ አንዳችም ፡ ለእኔ ፡ ማይገባ ፡ ነበር
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ አርገሃልና ፡ እደነቃለሁ
አብዝቼ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x)
ሙት ፡ ነበርሁ ፡ የማረባ
ከምንደሬ ፡ ስትገባ
ምን ፡ ነበረኝና ፡ ምኔን ፡ ወዶ ፡ ልበል
የትኛው ፡ እኔነቴ ፡ ለዚ ፡ ሳበው ፡ ልበል
እንዲያው ፡ ቸርነትህ ፡ ያ ፡ ፍቅርህ ፡ ካልሆነ
አይገባኝም ፡ መድሃኒቴ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የአንተ ፡ ውለታ (፪x)
አዝ፦ ከተደረግልኝ ፡ በጎነት ፡ አንዳችም ፡ ለእኔ ፡ ማይገባ ፡ ነበር
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ አርገሃልና ፡ እደነቃለሁ
አብዝቼ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя