እስኪ አክብሩልኝ የለወጠኝን የለወጠኝን
አዲስ ስም ሰጥቶ የቀየረኝን የቀየረኝን
ከማይጠፋው ዘር የወለደኝን የወለደኝን
ለቤቱ አገልጋይ ያደረገኝን ያደረገኝን
እኔም ላክብረው ባለው ዘመኔ
ላዳነኝ ለርሱ ለዚህ መድህኔ
ብዘምርለት ሁሌ ብናገር
አይበዛበትም ላረገው ነገር
ስንቱን አውርቼ የቱን ልተው ውለታው በዝቷል ውለታው በዝቷል
የማዳኑን ክንድ በእኔ ለፍጥረት ገልጧል ለፍጥረት ገልጧል
የእኔን መለወጥ ያየ ይበል አይበቃም ይበል አይበቃም
ገና እጁ አላጠረም ያድናል ሌላም ያድናል ሌላም
ክሩ በመርፌ የገባለት ሰው የገባለት ሰው
የዓይኑም እምባ ፈሶ የታበሰው ፈሶ የታበሰው
በሩጫ ሜዳ መስመር ከያዘ መስመር ከያዘ
ደካማው ሲወድቅ ብርቱው ካገዘ ብርቱው ካገዘ
በመከናወን ማን ቅር ይሰኛል
አእምሮ ከሌለው ግን ቅር ይለዋል
ማሰብ የሚችል አእምሮው ጤነኛ
መከናወንን ይወዳልና
ታዲያ ምነው ቅር አላችሁ ስይዝ መስመሩን ስይዝ መስመሩን
መከናወን ሲሆንልኝ ሲያወርሰኝ ክብሩን ሲያወርሰኝ ክብሩን
ከዚያ ከአስጨናቂው አለም ሳመልጥ በርሬ ሳመልጥ በርሬ
ተከትሎኝ መምጣት እንጂ አይጠቅምም ወሬ አይጠቅምም ወሬ
ዕድሜዬ ሲጨምር ዓመት ሲበዛ ዓመት ሲበዛ
ሲያሸጋግረኝ መስሎኝ የዋዛ መስሎኝ የዋዛ
ስቀልድባት በሕይወቴ ላይ በሕይወቴ ላይ
መቼ አስቻለው ሲያየኝ ከሰማይ ሲያየኝ ከሰማይ
ለካ አስቀድሞ አስቦኝ ኖሯል
የመለወጤ ጊዜያቱ ደርሷል
እርሱ የመደበው ሰዓቱ አያልፍ
ጌታ ኢየሱሴን አግኝቼው ሳላርፍ
እኔም አላለፍኩ ከቀኑ ተማረኩለት ተማረኩለት
የርሱ ፍቅር አይሎ እንጂ ምን አረኩለት ምን አረኩለት
ምን አይቶብኝ ነው እንዳልል ራሱን አይቶ ነው ራሱን አይቶ ነው
ለውጦ ከቀያየረኝ ከልካዩስ ማነው ከልካዩስ ማነው
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя