Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Keberigne текст песни

Исполнитель: Sofia Shibabaw

альбом: Fikir Kemekabir Belay, Vol.1


በጨለማ ፡ እያለሁ ፡ ነፍሴ ፡ ተንከራትታ ፡
መቼ ፡ ተውከኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
መቼ ፡ ተውከኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሆኜ ፡ የተጠቃሁ
አወጣኸኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
አወጣኸኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ብቻዬን ፡ ሳለቅስ ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ስጮህ ፡ ብዬ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ስጮህ ፡ ብዬ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ ደረስክ ፡ ሳትቆይ ፡ እስከማታ
ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ
ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር
ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል
ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር
ትንሽ ፡ ከቀለለኝ
ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ
ስላረግከው ፡ ተዓምር
ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ
በጠላቴ ፡ መንግስት ፡ በእቅዱ ፡ ውስጥ ፡ ሆኜ
አይተኸኛል ፡ መድኃኒቴ
አይተኸኛል ፡ መድኃኒቴ
አወጣኸኝ ፡ ከእጁ ፡ ሳትጠፋ ፡ ሕይወቴ
ክበርልኝ ፡ መድኃኒቴ
ክበርልኝ ፡ መድኃኒቴ
ልትጠቀምብኝ ፡ በኔ ፡ ልትሰራ
ፈልገህ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
ፈልገህ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
ነጥቀህ ፡ የታደግከኝ ፡ ከዚያ ፡ ባለ ፡ ጋራ
ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ
ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር
ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል
ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር
ትንሽ ፡ ከቀለለኝ
ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ
ስላረግከው ፡ ተዓምር
ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ
ለኃጥዕ ፡ ለጻድቅ ፡ ፀሐይህ ፡ ይወጣል
ለፍጥረትህ ፡ ሁሉ ፡ ይወጣል
ለፍጥረትህ ፡ ሁሉ ፡ ይወጣል
ቸርነትህ ፡ ፍቅርህ ፡ መች ፡ ይበላለጣል ፡
ለሁሉም ፡ ሰው ፡ ሰጥተኸዋል
ለሁሉም ፡ ሰው ፡ ሰጥተኸዋል
ለኔ ፡ ግን ፡ አወጣህ ፡ ብርሃን ፡ ሌላ ፡ ፀሐይ
ካልጠበቅኩት ፡ አቅጣጫ ፡ ላይ
ካልጠበቅኩት ፡ አቅጣጫ ፡ ላይ
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ወልድ ፡ ወረደ ፡ ከላይ
ክበርልኝ ፡ በምድር ፡ በሰማይ
ክበርልኝ ፡ በምድር ፡ በሰማይ
እኔ ፡ ያልዘመርኩኝ
ማን ፡ ይዘምርልህ ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር
ከቶ ፡ እንዲህ ፡ በቀላል
ተዘርዝሮ ፡ አያልቅም ፡ ምህረትህ ፡ ቢቆጠር
ትንሽ ፡ ከቀለለኝ
ብዬ ፡ እንጂ ፡ አያልቅም ፡ ብዘምር ፡ ባወራ
ስላረግከው ፡ ተዓምር
ስላሸጋገርከኝ ፡ ያንን ፡ ተራራ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители