የእኔን ሰው መሆን የፍጥረቴን ሚስጥር
የደመነፍስ ኑሮን ጠፍቶ ሚተረትር
የታረደለኝ በግ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዳለኝ ነገረኝ
እኔም ዝቅ ብዬ ልስገድለት ለእሱ ምሥጋና ነው ያለኝ
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምሥጋና ነው ያለኝ
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምሥጋና ነው ያለኝ
ተከተይኝ አለኝ ትምክቴን አስጥሎ
የዓለም አይደለሽም አንቺ የእኔ ነሽ ብሎ
አክብሮት አምልኮ ለሌላው ለመስጠት
ጉልበቶቼ ታጥፈው ሊንቀጠቀጡለት
እንዲህ አይደረግም እንዲህ አይደረግም
ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም
እንዲህ አይደረግም እንዲህ አይደረግም
ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም
ያልሳሳ ገበታን ጌታዬ አዘጋጅቶ
ከሕይወት ቃል ማዕድ መንፈሴን አርክቶ
እንዳዜም ካበቃኝ በሕያዋን ምድር
ልሰግድ ይገባኛል ከንጉሡ እግር ሥር
ይገባኛል ይገባኛል
አምላኬ እኮ እኔን ሌላ ሰው አርጐኛል
ይገባኛል ይገባኛል
አምላኬ እኮ እኔን ሌላ ሰው አርጐኛል
ከምድራዊው ኑሮ ያለፈ አለ ብሎ
የሞተልኝ ጌታ የእኔን እዳ ከፍሎ
ክርስቶስን ለበስኩ እንዴት አምሮብኛል
ክብሬና ሞገሴን ማን ያወልቅብኛል
እንዲህ አይደረግም እንዲህ አይደረግም
ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም
እንዲህ አይደረግም እንዲህ አይደረግም
ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም
የእኔን ሰው መሆን የፍጥረቴን ሚስጥር
የደመነፍስ ኑሮን ጠፍቶ ሚተረትር
የታረደለኝ በግ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዳለኝ ነገረኝ
እኔም ዝቅ ብዬ ልስገድለት ለእሱ ምሥጋና ነው ያለኝ
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምሥጋና ነው ያለኝ
እልልታ እልልታ እልልታ
እልልታ ነው ያለኝ
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምሥጋና ነው ያለኝ
እልልታ እልልታ እልልታ
እልልታ ነው ያለኝ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя