ተኝቶ እንደሚያልም ሰው በህልሙ እንደሚበላ ነው
ጣፋጭን እንደሚያልም ሰው በእንቅልፉ እንደሚጠጣ ነው
ግን ሌሊቱ አልፎ ከእንቅልፉ ሲነቃ
መሆኑን ይረዳል ከንቱ ህልም ብቻ
ግን ሌሊቱ አልፎ ከእንቅልፉ ሲነቃ
መሆኑን ይረዳል ከንቱ ህልም ብቻ
ከንቱ ህልም ብቻ የጠላቴ ዛቻ
ምኞቱ ቅዠቱ እስኪነጋ ሌቱ
ከንቱ ህልም ብቻ የጠላቴ ዛቻ
ምኞቱ ቅዠቱ እስኪነጋ ሌቱ
ከንቱ ህልም ብቻ የጠላቴ ዛቻ
ምኞቱ ቅዠት ነው የማይፈፀመው
ከንቱ ህልም ብቻ የጠላቴ ዛቻ
ምኞቱ ቅዠት ነው የማይፈፀመው
በጠላት ኀይል ላይ ሥልጣን ተሰጥቶኛል
እባብና ጊንጡን አስረግጦልኛል
የብረት መውጊያ ነው ከኔ ጋራ ያለው
ለሱ ይብስበታል ማንም ቢቃወመው
የሠራዊት ጌታ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው
ለሱ ይብስበታል ማንም ቢቃወመው
የሠራዊት ጌታ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው
ለሱ ይብስበታል ማንም ቢቃወመው
እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ይመስገን
ከጠላት ሀሳብ ያስመለጠን እግዚአብሔር ይመስገን
እግዚአብሔር ይባረክ እግዚአብሔር ይባረክ
ጠላታችንን ሚያንበረክክ እግዚአብሔር ይባረክ
በምኞት ሲማልል ቢኖርም ጠላቴ ከቶ አያገኘኝም
ቀን ከሌት ዙሪያዬን ቢዞርም ጠላቴ ከቶ አያገኘኝም
ጌታ ከልሎኛል በደሙ ሸፍኖ
ልጄ ሆይ አትፍሪ አለሁልሽ ብሎ
ጌታ ከልሎኛል በደሙ ሸፍኖ
ልጄ ሆይ አትፍሪ አለሁልሽ ብሎ
ከንቱ ህልም ብቻ የጠላቴ ዛቻ
ምኞቱ ቅዠቱ እስኪነጋ ሌቱ
ከንቱ ህልም ብቻ የጠላቴ ዛቻ
ምኞቱ ቅዠቱ እስኪነጋ ሌቱ
እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ይመስገን
ከጠላት ሀሳብ ያስመለጠን እግዚአብሔር ይመስገን
እግዚአብሔር ይባረክ እግዚአብሔር ይባረክ
ጠላታችንን ሚያንበረክክ እግዚአብሔር ይባረክ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя