Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Fetenelegne текст песни

Исполнитель: Sofia Shibabaw

альбом: Fetenelegne, Vol. 3


ህልምን ያሳየኸው ዮሴፍ ተጥሎ
ፍርድ ተጣሞበት በእስር ቤት ተረስቶ
አንተን የመጠበቅ ቢረዝምበት ጊዜው
ጠጅ አሳላፊውን አንተ አስበኝ አለው
ቀኑ ሲደርስ ግን በአንተ ተጎብኝቶ
በችኮላ አወጡት ፀሎቱ ተሰምቶ
ተለመነኝ ጌታዬ ሆይ ተለመነኝ
ፀሎቴ ወደ ጆሮህ ይድረስልኝ
ተለመነኝ አምላኬ ሆይ ተለመነኝ
ፀሎቴ ወደ ማደሪያህ ይድረስልኝ
ተለመነኝ ጌታዬ ሆይ ተለመነኝ
ልመናዬ ወደ ጆሮህ ይድረስልኝ
ተለመነኝ አምላኬ ሆይ ተለመነኝ
ፀሎቴ ወደማደሪያህ ይድረስልኝ

አቤቱ ልቤ ጨከነ አቤቱ ልቤ ጨከነ
አቤቱ ልቤ ጨከነ አቤቱ ልቤ ጨከነ
እግዚአብሔር ዐለቴ ኃይሌ ነው እያለ
ሰው ምን ያደርገኛል ከኔ ጋራ አለ
ልቤ ጨከነ
አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው
አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው
በአምላኬ በእግዚአብሔር ኃይሌን አድሳለው
ሰው ምን ያደርገኛል ጌታ ከኔ ጋር ነው
ልቤ ፅኑ ነው

ከ400 ዓመታት የጭቆና ስፍራ
ህዝብን እስራኤልን ከግብፅ ስታወጣ
የያዕቆብ አምላክ እያሉ ሲጮሁ
ፈጥነህ ታደካቸው ስምህን ሲጠሩ
የተቦካውን ሊጥ እንኳን ሳይጋግሩ
ከአንተ ጋር ሲወጣ ተሸክመው ወጡ
ፍጠንልኝ ጌታዬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ምህረትህ ብዛት ፍረድልኝ
ፍጠንልኝ አምላኬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ሀጢያቴ ከቶ አታርግብኝ
ፍጠንልኝ ጌታዬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ምህረትህ ብዛት ፍረድልኝ
ፍጠንልኝ አምላኬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ሀጢያቴ ከቶ አታርግብኝ

ፊትህን የሚሹ በእኔ አይነወሩ
ተስፋ የሚያደርጉ አይተውኝ አይፈሩ
በምህረትህ ፍትህ አርግልኝ ጌታዬ
ጉብኝትህ ይፍጠን በቤቴ በሀገሬ
ፍጠንልኝ ጌታዬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ምህረትህ ብዛት ፍረድልኝ
ፍጠንልኝ አምላኬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ሀጢያቴ ከቶ አታርግብኝ
ፍጠንልኝ ጌታዬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ምህረትህ ብዛት ፍረድልኝ
ፍጠንልኝ አምላኬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደ ሀጢያቴ ከቶ አታርግብኝ
አቤቱ ልቤ ጨከነ አቤቱ ልቤ ጨከነ
አቤቱ ልቤ ጨከነ አቤቱ ልቤ ጨከነ
እግዚአብሔር ዐለቴ ኃይሌ ነው እያለ
ሰው ምን ያደርገኛል ከኔ ጋራ አለ
ልቤ ጨከነ
አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው
አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው አቤቱ ልቤ ፅኑ ነው
በአምላኬ በእግዚአብሔር ኃይሌን አድሳለው
ሰው ምን ያደርገኛል ጌታ ከኔ ጋር ነው
ልቤ ፅኑ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители