አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል
ከአንደበቱ ፍሬ መልካሙን ይበላል
ሰነፍ ሰው በልቡ ስንፍናን ያወራል
በአንደበቱ ወጥቶ ስንቱን ሰው ያቆስላል
የጠቢብ ሰው ቃል ግን ጤና የሚሰጥ ነው
የጻድቁ አንደበት ሁሌም ለማነጽ ነው
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያት ይሸሻል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያት ይርቃል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀሜት ይሸሻል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከርኩሰት ይርቃል
አድነኝ አድነኝ አድነኝ አድነኝ
ከብርም ከወርቅም ጥበብህን ስጠኝ
አድነኝ አድነኝ አድነኝ አድነኝ
ከብርም ከወርቅም ማስተዋልን ስጠኝ
አድነኝ አድነኝ አድነኝ አድነኝ
አንተን እንድመስል ጌታ ሆይ ለውጠኝ
ወንድሙን የሚያማ የጌታን ህግ ያማል
በወንድሙ የሚፈርድ በአምላኩ ህግ ይፈርዳል
የሚቀጣ የሚምር ሥልጣን በእጁ ያለው
የሁሉ የበላይ እግዚአብሔር ብቻ ነው
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያት ይሸሻል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያት ይርቃል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀሜት ይሸሻል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከርኩሰት ይርቃል
እንጨትን አጋድሞ ጉድፍ ላውጣ ማይለው
የጠቢብ ሰው ዓይኖች በራሱ ላይ ናቸው
ልቡን እያሳተ አንደበቱን ሳይገታ
የሚያመልክ የሚመስለው አምልኮው ከንቱ ነው
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያት ይሸሻል
ሰነፉ ግን ታምኖ በራሱ ይኮራል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያተ ይሸሻል
ጠቢብ ሰው ይፈራል ከሀጢያት ይርቃል
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя