የሚያስፈራው ፡ ግርማህ ፡ ሲያበራ
ተንቀጠቀጠ ፡ ጨሰ ፡ ተራራ
የታላቅነትህ ፡ ክብር ፡ ሲያርፍበት
ሊቋቋም ፡ አልቻለም ፡ የአንተን ፡ ዉበት
አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡
አንተ ፡ ኃይለኛ
የሰልፉ ፡ አሸናፊ ፡ ሁሌም ፡ ፊተኛ
አንተ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡
አንተ ፡ ገናና ፡
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ባለዝና
ስምህን ፡ እባርካለው ፡ (፬X)
የአንተን ፡ ታላቅነት ፡ ሞገስን ፡ እያየው
ስምህን ፡ እባርካለው
አደራረግሀን ፡ ጥበብን ፡ እያየው ፡
ስምህን ፡ እባርካለው
ስምህን ፡ እባርካለው ፡ (፬X)
የአንተን ፡ ታላቅነት ፡ ሞገስን ፡ እያየው
ስምህን ፡ እባርካለው
አደራረግሀን ፡ ጥበብን ፡ እያየው ፡
ስምህን ፡ እባርካለው
አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡
አንተ ፡ ኃይለኛ
የሰልፉ ፡ አሸናፊ ፡ ሁሌም ፡ ፊተኛ
አንተ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡
አንተ ፡ ገናና ፡
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ባለዝና
የቃልህን ፡ ሥልጣን ፡ ያሳይ ፡ ፍጥረቱ
ውኃ ፡ ፈለቀ ፡ ወጣ ፡ ከአለቱ ፡
መልስን ፡ ይሰጥሃል ፡ ባሕር ፡ አድምጦ
ሕዝብህን ፡ ሊያሻግር ፡ ጠላትን ፡ ውጦ
አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡
አንተ ፡ ኃይለኛ
የሰልፉ ፡ አሸናፊ ፡ ሁሌም ፡ ፊተኛ
አንተ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡
አንተ ፡ ገናና ፡
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ባለዝና
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя