Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Gud Fela текст песни

Исполнитель: Dibekulu

альбом: Yetu Gar Neh?


ብራ ፀደይ ወጋገኔ
አትራቂቢኝ ነይ ወደ እኔ

ወይና ደጋ ደግ አመሌ
እንዳላጣሽ ጎኔ ሁሌ

ሁሉ መና ከአንቺ ውጪ ነው መባዘን
(ሁሉ መና ከአንቺ ውጪ ነው መባዘን)
በሽ ተድላ ለቤቱ የሆንሽ ማዕዘን
(በሽ ተድላ ለቤቱ የሆንሽ ማዕዘን)
አንቺን ሸጉጦ ኮራ ነው
የምን መመኘት የሌላ ሰው
ከስንት አጓጉል ምለየው
ሁሌም ምትሃት ስላየሁ
አንቺን ሸጉጦ ዘና ነው
የለም መመኘት የሌላ ሰው
ከስንቱ አጓጉል ተለየው
አንቺን ምትሃት እያየሁ
ወይ ወይ ወይ ወይ
ከአንቺ ውጪ ቤቴ
ተይ ተይ ተይ ተይ
አይሆንም በሞቴ
ነይ ነይ ነይ ነይ
ገዷ እመቤቴ
በገሃድ የታየ ድብቁ ብቃቴ
ጉድ ፈላ ጉድ ፈላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
አንጀቴን እየበላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ነይ መላ ነይ መላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
የለኝ ከአንቺ ሌላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ

ብራ ፀደይ ወጋገኔ
አትራቂቢኝ ነይ ወደ እኔ

ወይና ደጋ ደግ አመሌ
እንዳላጣሽ ጎኔ ሁሌ

ውብ ስብዕና በሽ በሽ ነው በተማመን
(ውብ ስብዕና በሽ በሽ ነው በተማመን)
ገና ገና ደማቂ እስኪሆን ሙሉ ቀን
(ገና ገና ደማቂ እስኪሆን ሙሉ ቀን)
አንቺን ሸጉጦ ቀብረር ነው
የምን ማቀርቀር ለየቱ ሰው
በአንቺ የመጣ ሞቴ ነው
አንድም ኩነኔ ወሬ የለው
አንቺን ሸጉጦ ቀና ነው
የምን ማቀርቀር ለየቱ ሰው
በአንቺ የመጣ ሞቴ ነው
ምንም ኩነኔ ወሬ የለው
ወይ ወይ ወይ ወይ
ከአንቺ ውጪ ቤቴ
ተይ ተይ ተይ ተይ
አይሆንም በሞቴ
ነይ ነይ ነይ ነይ
ገዷ እመቤቴ
በገሃድ የታየ ድብቁ ብቃቴ
ጉድ ፈላ ጉድ ፈላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
አንጀቴን እየበላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ነይ መላ ነይ መላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
የለኝ ከአንቺ ሌላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ጉድ ፈላ ጉድ ፈላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
አንጀቴን እየበላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ነይ መላ ነይ መላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
የለኝ ከአንቺ ሌላ ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ፍቅርሽ ጉድ አፈላ
ፍቅርሽ ጉድ አፈላ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители

Tsedi

Исполнитель