የጥንቱን ታሪኳን ስመራመርበት
ጥልቅ እውቀት አገኘሁ ፍቅሯን ስማርበት
ገና ወጣት ሳለች እንቡጥ ጽጌረዳ
ፍቅር አስተምራለች ያቺ ሰለስቴ አይዳ
የግብፁን ጦረኛ ጀግናው ራዳሚስ
በመልኳ ተጠልፎ ጥሎት የሷ ቀሚስ
ደምግባቷን ወዶ ሀገሩን ቢከዳ
አይዞህ አለሁልህ ብላዋለች አይዳ
ገራችው ሃይሉን ገራችው
በፍቅር አስተማረችው
እየራራችለት እሱንም አራርታው
ህዝቧን ነፃ አወጣች በውበት እረታው
አሸነፈኝ ብላ ቂምም ሳትይዝበት
ፈቀደች በፍቅር ልቧን እንዲያዝበት
ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ
የፍጥረት ንጋት የውብ ማለዳ
ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ
አርጎ የሰራት መልከ ፀዐዳ
♪
ቤቷ ልዕልት ሆና ንጉስ የወለዳት
ሎሌ አደረጏት እዛ በምርኮ ሲወስዷት
ከአገር የወጣ ሰው ክብር የለውም ብላ
ትንሽ መስላ ኖረች ሁሉን ተቀብላ
ገራችው ሃይሉን ገራችው
በፍቅር አስተማረችው
ገብቷት የሷን መውደድ መርጦ እንደተሰዋ
ከእሱ ጋር ጠጣችው መራራውን ጽዋ
ታሪኩን በደሟ ጠቅሳ ልትጽፍበት
ቆረጠች በፍቅሯ ሞቱን ልትሞትበት
ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ
ህይወቷን ሰጠች ለፍቅር ብላ
ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ
ተካፈለችው የነፍሱን እዳ
ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ
ተካፈለችው የነፍሱን እዳ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя